በድሬዳዋ አሁንም የፀጥታ ችግር አልተፈታም

0
958

በድሬዳዋ ከተማ አሁን የፀጥታው ችግር እንዳልተፈታ ምንጮች ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ። የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ጥቅምት 18 ለ19/2012 አጥቢያ ሌሊት ላይ በከተማዋ ከፍተኛ የሆነ የተኩስ ድምፅ መሰማቱን እና ማለዳ አካባቢ ረገብ ማለቱን የአዲስ ማለዳ ምንጮች አስታውቀዋል።

ገንደ ተስፋ እና መስቀለኛ በተባሉ አካባቢዎች ግጭቶች ያጋጠሙ ሲሆን በተለይም ደግሞ በድሬዳዋ ከተማ መስቀለኛ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተጠልለው በሚገኙ ሰዎች ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመፈፀሙ እና የአካባቢው ሰዎችም ጥቃቱን ለመከላከል ባደረጉት ጥረት ግጭት መቀስቀሱን እና መከላከያ መሐል በመግባት ማብረዱን ለማወቅ ተችሏል። ጥቃት አድራሾቹ ከድሬዳዋ ዙሪያ ገጠር ቀበሌዎች በመኪና ተጭነው መምጣታቸውን እና ድንገተኛ ጥቃት ማድረሳቸውን የአዲስ ማለዳ ምንጮች ይናገራሉ።

በግጭቱ የተጎዱ ሰዎች መኖራቸውንም የዓይን እማኞች አስታውቀዋል። መከላከያ ወደ ከተማዋ ሙሉ በሙሉ በመግባት ከተማዋን የማረጋጋት እና ግጭቶችን የመከላከል ስራ እየሰራ እንደሚገኝም ምንጮች ከስፍራው ገልፀዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here