የኢንሹራንስ ወር ሊከበር ነው

0
591

በ2015 የመጀመሪያው የኢንሹራንስ ወር “ጠንካራ የኢንሹራንስ ኢንደስትሪ ለአገር ኢኮኖሚ ግንባታ” በሚል መሪ ቃል ይታሰባል ተብሏል።

ረቡዕ ጥቅምት 02/2015 በኢሌሌ ሆቴል በተሰጠ መግለጫ፤ <የኢንሹራንስ ወር> በሚል መርህ ተዘጋጅቶ ከጥቅምት 5 ቀን 2015 ጀምሮ በየሳምንቱ ቅዳሜ የሚካሄድና ለአንድ ወር የሚቆይ የውይይትና የልምድ ልውውጥ መድረክ እንደሚኖር ተነግሯል።

የጌጤነሽ ኃይለማርያም እና ብርሃን ተስፋዬ ኢንሹራንስ ብሮከርስ የኅብረት ሽርክና ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ጌጤነሽ ኃይለማሪያም ባደረጉት ንግግር፤ የኢንሹራንስ ወር ዝግጅቱ ኢንሹራንስ ድርጅቶች ውጤታማ መሆን የሚችሉበትን አውድ ለመፍጠር ያስችላል በሚል እምነት ነው የተዘጋጀው። ባለሞያዎች ሊያነሱና ሊያስገነዝቡ የሚፈልጓቸው ጉዳዮችም በሚኖሩት ተከታታይ መድረኮች ይነሳሉ ብለዋል።

‹‹የተወሰነ ካልሆነ በቀር ኅብረተሰቡ ስለኢንሹራንስ ግንዛቤው ዝቅተኛ ነው። ለምን ኢንሹራንስ አልሰረፀም ለምን ሰው ራቀ የሚለውንና አሉታዊውን አመለካከት ለመቀየር ምን እናድርግ ብለን፣ ተደራሽነቱ ለምን ጎደለ የሚለውን ለማሳየትና ግንዛቤ ለመፍጠር መቆስቆሻ ነው።›› ሲሉም ስለዝግጅቱ አስፈላጊነት አስረድተዋል።

‹‹40 የሚደርሱ የዋስትና ዓይነቶች አሉ። ግን በአስገዳጅነት ያሉ ዋስትናዎች ናቸው የሚተገበሩት›› ያሉት ጌጤነሽ፣ በአሁኑ ወቅት የኢንሹራንስ ዘርፉን የበለጠ ለመደገፍ እና ለማነቃቃት ከዘርፉ የበቁ ባለሙያዎችን በማካተትና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን “የኢንሹራንስ ወር” በየዓመቱ እንዲከበር በመሥራት ላይ እንገኛለን ብለዋል።

ጌጤነሽ ኃ/ማርያምና ብርሃን ተስፋዬ የመድን ሥራ አዋዋይና አማካሪ የተመሠረተበትን የ25ኛ ዓመት ክብረ በዓል ለማክበር በተቋሙ የፕሮግራሙ ሐሳብ አመንጪነት የተዘጋጀ ሲሆን፤ መድረኩ በዓይነቱ የመጀመሪያ ከመሆኑም በተጨማሪ በቀጣይነትም በየዓመቱ በተመሳሳይ መልኩ ዝግጅት ለማድረግ ታቅዷል ተብሏል።


ቅጽ 4 ቁጥር 206 ጥቅምት 5 2015

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here