በአርጎባ ብሔረሰብ እና በአጎራባች የአፋር ክልል ነዋሪዎች መካከል የእርቀ ሰላም መድረክ ተካሄደ

0
857

በአማራ ክልል አርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳና በአፋር ክልል ተላላክ ወረዳ የኅብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ተፈጥሮ የነበረውን አለመግባባት በዘላቂነት ለመፍታት የኹለቱ አጎራባች ሕዝቦች እርቅ በመፈጸምና ይቅርታ በመደራረግ አንድነትንና የነበሩ እሴቶችን ይበልጥ ለማጠናከር የጋራ መድረክ በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ መዲና ከተማ ተካሂዷል።

የኹለቱ አጎራባች ሕዝቦች ለዘመናት ጠብቀው ያቆዩዋቸውን የአብሮነት፣ የሰላም፣ የመቻቻልና የመከባበር እሴቶችን ቀድሞ ወደነበረበት መመለስና አጠናክሮ መቀጠል ይኖርባቸዋል ሲሉ የኹለቱም አጎራባች ወረዳ የአገር ሽማግሌዎችና የሐይማኖት አባቶች በእርቅ ሥርዓቱ ላይ ተናግረዋል።

እርስ በርስ የሚከባበርና በይቅር ባይነት የሚያምኑ ሕዝቦች ናቸው ያሉት የአገር ሽማግሌዎቹና የሐይማኖት አባቶቹ፣ እነዚህ ድንቅ የሕዝብ ነባር እሴቶች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል።

የኹለቱ አጎራባች ወረዳ ሕዝቦች ተከባብረውና ተፋቅረው ለረጅም ጊዜ የኖሩ፣ የተዋለዱና የተዛመዱ ስለመሆናቸው ተገልጿል።

በኹለቱ አጎራባች ወረዳ ሕዝቦች የሚካሄደው የእርቅ መድረክ የሕዝብ ለሕዝብ መልካም ግንኙነትን በማጠናከር የኹለቱን ሕዝቦች ሰላምና አንድነት በዘላቂነት ለማጽናት ያለመ ስለመሆኑ ተመላክቷል።

እንዲሁም በኅብረተሰቡ መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችና ግጭቶች ጉዳት ሳያደርሱ በራስ ባህልና ወግ መሠረት ለመፍታት መሰል መድረኮችን አጠናክሮ ማስቀጠል ተገቢ ነው ተብሏል። በኹለቱ አጎራባች ወረዳ ሕዝቦች መካከል የነበረውን አለመግባባት ይቅር በመባባል ባለ10 ነጥብ አቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።


ቅጽ 4 ቁጥር 206 ጥቅምት 5 2015

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here