10ቱ የመጸዳጃ ቤትና ንጽህና መጠበቂያ እጥረት የከፋባቸው አገራት

0
551

ምንጭ፡-ወተር ኤድ ሪፖርት 2018

‹‹ወተር ኤድ›› የተሰኘው ድርጅት ይህን የጥናት ሪፖርት ያወጣው በቅርቡ The Crisis in the Classroom: The State of the World’s Toilets 2018 በሚል ርዕስ ሲሆን መረጃዎቹን በአውሮፓዊያኑ የዘመን ቀመር 2015 እንደሰበሰባቸው አመልክቷል ፡፡
የንጽህና መጠበቂያ እጥረት ቀውስ በትምህርት ቤቶች ብቻ ተወስኖ ያለ አለመሆኑን የሚያመለክተው ይኸው ሪፖርት ከሰሃራ በታች ባሉ አገራት 344 ሚሊዮን የሚገመቱ ሕጻናት በቂ (ተገቢ) መጸዳጃ ቤት እንደሌላቸው ጠቅሷል፡፡ ይህ ከእንግሊዝ፣ አየርላንድ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ስዊዘርላንድ፣ ጣሊያን፣ ስፔንና ፖርቹጋል ሕዝቦች ድምር የሚስተካከል ስለመሆኑ ሪፖርቱ አትቷል፡፡
በትምህርት ቤቶች የመጸዳጃ አቅርቦት እጥረት የመጀመሪያ የሆነችው ኢትዮጵያ ነዋሪዎች በቤታቸው በቂ መጸዳጃ ቤት ለማግኘት የሚፈተኑባት አገር መሆኗንም አልደበቀም፡፡
በአገሪቱ በደካማ የንጽህና አጠባበቅና ቆሻሻ ውኃ አማካይነት በየዓመቱ በአማካይ ስምንት ሺህ 500 ሕጻናት እንደሚሞቱም ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here