ረዳት ኮሚሽነር ሰዒድ አሕመድ በዋስ ተለቀቁ

0
697

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የኮሙዩኒኬሽንና ሚዲያ መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ሰዒድ አሕመድ   ሰኔ 15/2011በክልሉ በተከሰተው የከፍተኛ አመራሮች ግድያ እጃቸው አለበት በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው  ምርመራ ሲጣራባቸው ቆይቶ ዛሬ ጥቅምት 20/2012 በዋስ መለቀቃቸውን የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

የምርመራ መዝገቡ በጥቅምት 18/2012 ለክልሉ ዐቃቤ ሕግ የተላከ ሲሆን እስካሁን ባለው የምርመራ ውጤት ግድያውን ለመምራታቸውም ሆነ ለመሳተፋቸው በቂ መረጃ ባለመገኘቱ የባህረዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በ ጥቅምት 20/2012  በዋለው ችሎት ዐቃቤ ሕግ የዋስትና አስተያየት እንዲሰጥ በተጠየቀው መሰረት የተጠርጣሪው የዋስትና ጥያቄ የማይቃወም መሆኑን የገለፀ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት ከዐቃቤ ሕግ የተሠጠውን የውሳኔ አስተያየት መሰረት በማድረግ በ10 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ወስኗል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here