ሚሊዮን ማቲዎስ የትምህርት ሚንስቴር ሚንስትር ዲኤታ ሆነው ተሾሙ

0
738

የቀድሞው የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር የነበሩት እና ክልሉን ለአንድ ዓመት የመሩት ሚሊዮን ማቲዎስ የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ ሆነው መሾማቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል።

ትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሀረጓ ማሞ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት የሚሊዮን ማቲዎስ የሹመት ደብዳቤ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መድረሱን እና በቅርቡም ስራ እንደሚጀምሩ አረጋግጠዋል። በሰባተኛው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መደበኛ ጉባኤ ላይ ደቡብ ክልልን እንዲመሩ የተመረጡት ሚሊዮን ማቲዎስ በጊዜው ደቡብ ክልልን ይመሩ የነበሩትን ደሴ ዳልኬን በመተካት ነበር ወደ ስልጣን የመጡት።

ሚሊዮን ማቲዎስ የአንድ ዓመት ክልሉን የማስተዳደር ጉዞም በነሐሴ 2012 ተገቶ በምትካቸው ርስቱ ይርዳው የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ተሹመዋል።

 

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here