ዕረቡ ጥቅምት 16 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የአገር መከላከያ ሰራዊት ኮረም ከተማን ሲቆጣጠር የኮረም ከተማ አንበሳ ባንክ ሥራ አስኪያጅ ከላሊ አብርሃና ምክትል ሥራ አስኪያጅ ደሳለኝ ደረስ ከህወሓት ቡድን ጋር በመሆን የባንኩን ገንዘብ ማለትም፤ 6 መቶ 21 ሺሕ 460 ብር ፣ 6 ሺሕ 146 የአሜሪካ ዶላር እና 1 መቶ 90 ዩሮ ይዘው ሊጠፉ ሲሉ በቦታው በነበርው በአገር መከላከያ ሰራዊት በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ።
ሃላፊዎቹ ገንዘቡን ይዘው ሊጠፉ የነበረው ገና የአገር መከላከያ ሰራዊት ኮረም እንዳልገባ በመገመት እንደሆነ በቦታው የተገኙ እማኞች መናገራቸው በዘገባው ተጠቁሟል፡፡
ሊዘረፍ የነበረው ገንዘብ በአካባቢው በተመረጡ የአገር ሽማግሌዎች እና የከተማው ፖሊስ አማካኝነት ወደ ባንኩ ገቢ እንዲሆን መደረጉን ከኮረም ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡



