የቦይንግ ስራ አስፈጻሚ በአሜሪካ ህዝብ እንደራሴ ፊት በመቅረብ የማስተባበያ ቃላቸውን ሰጡ

0
534

ለ 346 ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት በሆነው የቦይንግ ሰባት ሰላሳ ሰባት ማክስ ኤይት መከስሰክ በኋላ የአምራች ኩባኒያው ፕሬዝደንት ዴኒስ ሙሊንበርግ በአሜሪካ የህዝብ እንደራሴ ምክር ቤት ፊት ቀርበው ለመጀመሪያ ግዜ ቃላቸውን ሰተዋል።

የቦይንግ የበረራ መቆጣጠሪያ ሁለቱ አደጋዎች በሚከሰቱበት ወቅት መቆጣጠሪያ በአግባቡ ይሰራ እንዳልነበር እንደሚያውቅ የብሄራዊ ትራንስፖርት ደህንነት ቦርድ ሊቀመንበር ሮበርት ሰምዋልት ለእንደራሴው አስረድተዋል።

እንደ አውሮፕላን አምራች የመቆጣጠሪያ ስርዓቱ ስለመስራቱ እርግጠኛ መሆን እንደነበረባቸው ዋና ስራ አስፈፃሚው ለሴኔቱ አምነው ተናግዋል። ችግሩን ተመልክተናል የሚሉት ሃላፊው አውሮፓላኑን የተሰጠውን ፈቃድ ደጋግመው እንደሚመለከቱ በመግለጽ የደህንነት ጉዳዩን በሚመለከት ግን የፌደራል አቬሽን ባለስልጣን ለቦይንግ ከወራት በፊት ትዕዛዝ እንደሰጠ ገልጸዋል።

የቀድሞ የብሄራዊ ትራንስፖርተ ደህንነት ቦርድ ሊቀመንበር በሚመሩት የጋራ የቴክኒክ ጥናት ባለስልጣኑ አብራሪዎች ስለ ቦይንግ እንዲሰለጥኑ ባለመደረጉ እንዴት ለአውሮፕላኑ ፍቃድ እንደተሰጠ እየመረመሩ መሆናቸውን አንስተዋል።

ቦይንግ ባደረገው የውስጥ ፍተሻ ስህተቶች እንደነበሩበት ኢንጅነሮቹ ከመግለጽ አልተቆጠቡም። የቦይንግ የንግድ አየር መንገድ መሪ ኢንጅነር እንደሚሉት ኩባንያው የነበሩበትን ስህተቶች በግልጽ ባለማስቀመጡ ቦይንግ ሰባት ሰላሳ ሰባት ማክስ ኤይት እንዲወድቅ ምክንያት እንደሆነ አስረድተዋል።

በላዮን ኤርም ሆነ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ያጋጠሙት አደጋዎች የአውሮፕላኑን አፍንጫ ወደ ታች እንዲዘፍቅ የሚያደርግ እንደሆነ እሚገልጽ እንደነበር ይህም አብራሪዎች አውሮፕላኑን በአፍንጫ ከመውደቅ ለመታደግ የሚያደርጉት ጥረት ያከሸፈ እንዳደረገባቸው ይገልጻሉ።

የቦይንግ ዋና ስራ አስፈጻሚ የተጎጂ ቤተሰቦችን ይቅርታ በመጠየቅ ወገኖቻቸውን ላጡ ሀዘናቸው ከባድ መሆኑን አንስተዋል።
በመሆኑም ቦይንግ ባለፈው አመት ጥር እንዲሁም መጋቢት ላይ ለተከሰከሱት አውሮፕላኖች ወገኖቻቸውን ላጡ ተጎጂ ቤተሰቦች የ አንድ መቶ ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደሚያደርግም ይፋ አድርገዋል። በኢትዮጵያ አየር መንግድ ተጎጂ የሆኑ ሃያ ቤተሰብ አባሎች በቀጥታ ስራ አስፈጻሚው ሲናገሩም ተመልክተዋቸዋል።

ስራ አስፈጻሚው ከስራቸው ለመነሳት ዕቅድ ካላቸው ተብለው ለተጠየቁበት አሁን ሃሳባቸው የአየር መንገዱን ደህንነት ለመጠበቅ መስራት መሆኑን አስታውቀዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 52 ጥቅምት 22 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here