መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናየቡሌ ምርጫ ክልል የድጋሚ ምርጫ ከደቡብ ክልል ከሚካሄደው ሕዝበ ውሣኔ ጋር በአንድ...

የቡሌ ምርጫ ክልል የድጋሚ ምርጫ ከደቡብ ክልል ከሚካሄደው ሕዝበ ውሣኔ ጋር በአንድ መርኅ ግብር እንዲከናወን ተወሰነ

ረቡዕ ኀዳር 14 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛውን አገራዊ ምርጫ ሰኔ 14 ቀን 2013 እና መስከረም 20 ቀን 2014 በኹለት ዙር ማከናወኑ ይታወቃል።

ቦርዱ በተያዘው በጀት ዓመት በተለያዩ ምክንያቶች 6ኛው አገራዊ ምርጫ ባልተካሄዱባቸው የተወሠኑ የምርጫ ክልሎች ላይ ምርጫ ለማከናወን የቅድመ ዝግጅቶች ሥራዎችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ቀደም ሲል ቦርዱ 6ኛውን አገራዊ ምርጫ ካካሄደባቸው ምርጫ ክልሎች አንዱ በሆነው በቡሌ ምርጫ ክልል የተካሄደው አገራዊ ምርጫ ላይ መጠነ ሰፊ የሕግ ጥሰት እንደነበር በማረጋገጡ፤ ምርጫው በድጋሚ እንዲከናወን ጥቅምት 19 ቀን 2014 መወሠኑም ይታወሳል።

ይህንንም የድጋሜ ምርጫ በተያዘው ዓመት በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ ከሚካሄደው ሕዝበ ውሣኔ ጋር በአንድ መርኅ ግብር ጥር 29 ቀን 2015 አብሮ እንዲከናወን ኅዳር 03 ቀን 2015 መወሰኑን ቦርዱ አስታውቋል።

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች