14 ሚሊዮን የመናዊያን ለረሃብ እየተጋለጡ ነው
በአስከፊ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ በምትገኘው የመን በሦስት ዓመት ውስጥ 85 ሺህ የሚጠጉ ሕጻናት በረሃብ ምክንያት ሕወታቸውን እንዳጡ ተገለጸ፡፡
የሕጻናት አድን ድርጅት (ሴቭ ዘ ቺልድረን) የተባሩት መንግሰታትን መረጃ ተንትኖ ያወጣው ሪፖርት እንዳመላከተው ከአውሮፓዊኑ ሚያዚያ 2015 እስከ ጥቅምት 2018 ድረስ 84 ሺህ 701 የመናዊን ሕጻናት በከፋው ረሃብ ህወታቸውን አጥተዋል፡፡ ባሳለፍነው ረቡዕ ይፋ የተደረገው ሪፖርት ጦርነቱ ከተከሰተ ጀምሮ ሕይወታቸውን ካጡት 85 ሺህ የመናዊን መካከል የአብዛኞቹ እድሜ ከአምስት ዓመት በታች መሆኑንም ጠቁሟል፡፡ በእርስ በርስ ጦርነት በምትናጠው የመን አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረግ ፈተናዎች መብዛታቸውም በለጋሽ ድርጅቶች ተደጋጋሚ ሪፖርቶች ተመላክቷል፡፡ ከፈተናዎቹ መካከል ያለው አለመረጋጋት ለጋሾች እንደፈለጉ ተንቀሳቅሰው የነፍስ አድን እርዳታን እንዳያደርሱ ማድረጉ ይገኝበታል፡፡ ይህም ለየመናዊያንን ‹‹በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ›› እንዲሉ ተጨማሪ ቅጣት ሆኖባቸዋል፡፡
የሳዑዲ አረቢያ መራሹ ጥምር ጦር ከአውሮፓዊያኑ መጋቢት 2015 ጀምሮ በየመን ጦርነት ጣልቃ መግባቱን ተከትሎ በሁዳይዳህ ወደብ በኩል ይገባ ከነበረው የምግብ እርዳታ በወር ከ55 ሺህ ቶን በላይ ቅናሽ እንዲከተል አስገድዷል፡፡ በወደቡ የገቢ ምርት መቀነስ የቀረው ይኸው ድጋፍ ሁለት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሕጻናትን ጨምሮ ለአራት ነጥብ አራት ሚሊዮን ሰዎች ጋፍ ይበቃ ነበርም ተብሏል፡፡
የዓለም ምግብ ፕሮግራም እንዳመለከተው ሁዳይዳህ ዋኛ የጦር ቀጣና መሆኑን ተከትሎ አሁን ላይ 14 ሚሊዮን የመናዊያን ለረሃብ እየተጋለጡ ነው፡፡
ከረሃቡ ባሻገር በየጊዜው የሚነሱ ወረርሽኞችም የየመናዊያን ስቃይ አበርች ሆነዋል፡፡
ከአረቡ አለም የፀደይ ዐብዮት ጋር ትስስር ያለው የየመን የእርስ በእርስ ጦርነት መንግስት በንግስት በነዳጅ ላይ ያደርግ የነበረውን ድጎማ በከፍተኛ መጠን መቀነሱን ተከትሎ በ2014 ክረምት መቀስቀሱ ይታወሳል፡፡