የ16 ዓመቷ ታዳጊ በፌስቡክ ጨረታ ተዳረች

0
775

ፌስቡክ በደቡብ ሱዳን የሚገኙ አንድ ሰው በማኅበራዊው ድረገጹ አንዲት የ16 ዓመት ታዳጊ ልጅን አጫርተው ሲሸጡ ምንም እርምጃ ስላልወሰደ ወቀሳ ደርሶበታል። ሰውየው ልጅቷን ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበልኝ ሰው እድራለሁ ብለው በፌስቡክ ገጻቸው ጽፈው 5 ሰዎች የተሳተፉበት ጨረታ ተካሒዷል ብሎ ሲ.ኤን.ኤን ዘግቧል። ባለፈው ሳምንት ሰውየው የልጅቷ ዘመድ ሳይሆኑ የምትኖርበት አካባቢ ነዋሪ መሆናቸው ታውቋል።
ፌስቡክ የጨረታውን ጽሑፍ አግኝቶ ያስወገደው ግን ልጅቷ ከተዳረች ከሳምንት በኋላ መሆኑም ተነግሯዋል። ጨረታው ላይ ከተሳተፉት ሰዎች መካከል ከፍተኛ የደቡብ ሱዳን መንግሥት ባለሥልጣንትም ይገኙ ነበረ። ልጅቷ ለማን እንደተዳረች ባይታወቅም ጨረታውን ያሸነፈው ሰው ለልጅቷ ቤተሰቦች 500 ከብቶች፤ ሦስት መኪናዎችና ዐሥር ሺሕ የአሜሪካ ዶላር እንደተከፈላቸው ፕላን ኢንተርናሽናል ተናግሯል። በደቡብ ሱዳን ካሉት ከ20-24 ዓመት የዕድሜ ገደብ ውስጥ ካሉት ሴቶች ሃምሳ በመቶ 18 ዓመት ሳይሞላቸው ተድረዋል። በአገሩ ባሕል አንዲት ልጅ ስትዳር በጥሎሽዋ መደራደር ቢኖርም የዘመኑ ቴክኖሎጂ ይህንን ዓይነት ጨረታን ሊያበረታታ መቻሉ ተነግሯል።
የፌስቡክ ቃል አቀባዮች ስለ ጨረታው መረጃ እንደደረሳቸው ከገጹ ላይ አንስተው እና አድራሻውን ሙሉ በሙለ አጥፍተዋል። ነገር ግን ብዙ የሴቶችና የሕፃናት መብት አራማጆች የፌስቡክ መልስ በመዘግየቱ የዚህች ልጅ ቤተሰቦች ያገኙትን ዋጋ ሲያዩ ሌሎች ዕድሜያቸው ያልደረሱ ልጆችን በተመሳሳይ ሊሸጡና ያለዕድሜያቸውም ሊድሩ ይችላሉ ብለው እንደተናገሩ ሲኤንኤን ዘግቧል።
ፌስቡክ በበኩሉ የጥበቃ ሥራውን በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥሉና በጥበቃ ላይ የተሠማራውን የሰው ኃይላቸውን በእጥፍ እንደሚያሳድጉ ተጋግረዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here