ግብጹ ፕሬዘዳንት በኅዳሴው ግድብ ዙሪያ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ተወያዩ

0
1124

የግብጹ ፕሬዘዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ኢትዮጵያ በኣባይ ወንዝ ላይ እየገነባች ያለውን ታላቁን የኅዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ በሚመለከት ከአሜሪካው አቻቸው ጋር ተወያዩ። ሰኞ ጥቅምት 24/2012 በአሜሪካ ዋሽግተን የተገናኙት ኹለቱ መሪዎች ከግብጽ ወገን ሦስተኛ አደራዳሪ አካል እንዲገባ ያቀረበችውን ሃሳብ ተከትሎ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

ትራምፕ በበኩላቸው አገራቸው ሦስቱ የዓባይ የላይኛው ተፋሰስ አገራት ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የሚያደርጉትን ድርድር እንደምትደግፍ እና ጋራ መግባባት ላይ እንዲደርሱም ምኞታቸው እንደሆነ አስታውቀዋል። ግብጽ የኅዳሴው ግድብ ግንባታን ተከትሎ የምታገኘው የውሃ መጠን እንደሚቀንስ ስጋቷን በይፋ ስትገልጽ መቆየቷ የሚታወስ ነው።

እንደ ግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሳሜህ ሽኩሪ ገለጻ የትራምፕ አስተዳደር ሦስቱን ኣባይ ተፋሰስ አገራትን ጥቅምት 26/2012 በአሜሪካ ዋሽንግተን እንዲገናኙ እና አለመግባባታቸውን እንዲፈቱ ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here