ተመራማሪ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ዶ/ ቦጋለች ገብሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

0
776

የሴት ልጅ ግርዛት ለማስቀረትና በሙያቸውም በርካታ ምርምር ስራዎችን ሲያከናውኑ የነበሩት ዶክተር ቦጋለች ገብሬ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። በአሜሪካን አገር ሕክምናቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ዶክተር ቦጋለች ሰኞ ጥቅምት 24/2012 ሌሊት ሕይወታቸው ማለፉን ለማወቅ ተችሏል።

በደቡብ ክልል ከምባታ ጠንባሮ ዞን የተወለዱት ዶክተር ቦጋለች የእናቶችንና የሕፃናትን ሞት መቀነስ እንዲሁም በአካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማትን በተመለከተ በርካታ ስራዎችን በመስራት አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግበዋል። ለሕዝብ እና ለአገር ያበረከቱትን በጎ ተግባር ተከትሎም በ2008 ዓመታዊ የበጎ ሰው ሽልማት አሸናፊ አንደነበሩም ኢቢሲ ዘግቧል።

በፈረንጆች 1998 የተጀመረውን ኬጂኤም የተሰኘውን እና አትራፊ ያልሆ ድርጅትን በዋና ስራ አስፈፃሚነት በመምራት እስከ ህልፈተ ሕይወታቸው መዝለቃቸውን ሕይወት ታሪካቸው ያስረዳል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here