ዳሰሳ ዘ ማለዳ ጥቅምት 25/2012

0
510

1-በቻይና ባለሀብቶች የተሰራው አዲስ አበባ ሲልክ ሮድ አጠቃላይ ሆስፒታል ጥቅምት 25/2012 ተመርቋል።ሆስፒታሉ በአንዴ 100 የህመምተኞችን አስተኝቶ ማከም የሚችል አቅም ያለዉና ደረጃውን የጠበቀ የቀዶ ጥገና ሕክምና በተለይም የጭንቅላት እና የኅብረሰረሰር ቀዶ ጥገና ላይ ስፔሻላይዝድ ባደረጉ ሐኪሞች አገልግሎት እንደሚሰጥ የጤና ሚኒስትሩ አሚር አማን ገልጸዋል።የሆስፒታሉ በ920 ሚሊዮን ብር የተገነባ ሲሆን በ13 ወራት ውስጥ ተሰርቶ መጠናቀቁን ሚኒስትሩ ተናግረዋል። (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………..

2-ኢትዮጵያ ኢንተርኔት በመጠቀም ነጻነት ካላቸዉ 65 አገራት ከፍተኛ መሻሻል ያሳየች አገር መሆኗን ፍሪደም ሐዉስ የተባለ ዓለም አቀፍ ተቋም አሰታወቀ።ኢትዮጵያ በኢንተርኔት ላይ ጥላቸው የነበሩ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ ሕጋዊ ገደብ ጥሎ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመነሳቱ ትልቅ ለዉጥ ማሳየቷን ተገልጿል።ፍሪደም ሐውስ ጥናት ካደረገባቸዉ 65 አገራት መካከል 33 የኢንተርኔት ነጻነት ማሽቆልቆል የተመዘገበ ሲሆን ከፍተኛ ማሽቆልቆል ታይቶባቸዋል ከተባሉት አገራት መካከል ሱዳን እና ሌላኛዋ አፍሪካዊት አገር ዚምባቡዌ ይገኙበታል። ካዛክስታን፣ ብራዚል እና ባንግላዴሽም መጥፎ ውጤት ካስመዘገቡት ውስጥ ተካትተዋል።(ዶቼ ቬሌ)

……………………………………………………………..

3-የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው አምስተኛ ዓመት የስራ ዘመን ሶስተኛ መደበኛ ስብሰባው ከ980 ሚሊዮን ዶላር በላይ የብድር ስምምነቶችን አጸደቀ።የብድር ስምምነቱ ከፈረንሳይ የልማት ኤጄንሲ፣ ከኮሪያ ኤክስፖርትና ኢምፖርት ባንክ፣ ከአረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት፣ ከነዳጅ አምራችና ላኪ አገራት ፈንድ እንዲሁም ከዓለም አቀፍ የልማት ማህበር ጋር ተፈራርመዋል።(ኢዜአ)

……………………………………………………………..

4-የሲዳማ ዞን ሕዝበ ውስኔ ምርጫ ለማስፈጸም ወደ ቦታው ያቀኑ አስፈጻሚዎች በሐዋሳ እየተንገላቱ መሆኑን ተናገሩ።የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ ሕዝበ ውሳኔ የድምፅ ሰጪዎች ምዝገባ ጥቅምት 26 ጀምሮ እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን ሕዝበ ውሳኔው ደግሞ ህዳር 10/2012 እንደሚካሄድ ቀን ተቆርጦለታል።ሕዝበ ውሳኔውን በበላይነት የሚያስፈፅመው የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከ6ሺህ የሚልቁ የምርጫ አስፈጻሚዎችምን ትላንት ወደ ሀዋሳ ከተማና የሲዳማ ወረዳዎች ልኳል።ተመልምለው ወደ ሀዋሳ ከተላኩት የምርጫ አስፈጻሚዎች ከ400 የሚልቁ አስፈጻሚዎች አሁንም በሀዋሳ ከተማ እንግልት እየደረሰባቸው እንደሆን ገልጸዋል።(ኢትዮ ኤፍ ኤም )

……………………………………………………………..

5 ኮተቤ መሳለሚያ በሚባል አካባቢ በመኖሪያ ቤቱ ብሬን (የመትረየስ ጠመንጃ) የሆነ የቡድን የጦር መሳሪያ ከመሰል 83 ጥይት እና 30 የሽጉጥ ጥይቶችን ሸሽጎ ለመሸጥ ሲያስማማ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሔደበት መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………..

6- ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት እሴት የተጨመረበት 166 ቶን ቡና ወደ ውጭ በመላክ ከ1ሚሊዮን 130 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡ (ኢቢሲ)

……………………………………………………………..

7-በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን የአንበጣ መንጋ ድጋሚ መከሰቱን እና ለመቆጣጠርም ጥረት እየተደረገ መሆኑን የኦፍላ ወረዳ ግብርናና ገጠር ልማት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ (ኢዜአ)

……………………………………………………………..

8-የባሌ ተራሮች ከ47ሺህ ዓመት በፊት የጥንታዊ የሰዎች መኖሪያ እንደነበር በተራራው የተገኙ የአርኪኦሎጂካል ቅርሶች ጥናት ማረጋገጥ ችሏል ተባለ፡፡ (ኢቢሲ)

……………………………………………………………..

9-በሶማሌ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገራዊ፣ በክልላዊና በሌሎች የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን ተናገሩ ። (ኢቢሲ)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here