ኦሮሚያ ውስጥ ያለ በቂ ስልጠና ወደ ሥራ የገቡ ዳኞች ለሥልጠና ተጠሩ

0
1060

የኦሮሚያ የፍትሕ አካላት ማሰልጠኛ እና የሕግ ምርምር ኢኒስቲቲውት ከሐምሌ 2009 እስከ መስከረም 2010 አሰልጥኗቸው በዳኝነት እና ዐቃቢ ሕግነት የሥራ መደብ ተሰማርተው ነበሩ ግለሰቦችን ለተጨማሪ ሥልጠና መጥራቱን የአዲስ ማለዳ ምንጮች ተናገሩ፡፡
በ2009 በርካታ ዳኞች በዲሲፕሊን ምክንያት ከሥራ መነሳታቸውን ተከትሎ ተቋሙ በጊዜው ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተመርቀው የወጡ የሕግ ባለሙያዎችን ለሁለት ወራት በማሰልጠን ወደ ሥራ አሰማርቶ የነበረ ሲሆን የኢኒስቲቲውቱ ማቋቋሚያ ደንብ በሚያዘው መሠረት ለአምስት ወራት ባለመሰልጠናቸው ምክንያት በሕጉ መሠረት ዳኛ ሁነው ሳይሾሙ አንድ ዓመት ገደማ አገልግለዋል፡፡ ይሁንና የቀራቸውን ሦስት ወራት ስልጠናን እንዲከታተሉ ከሥራ ገበታቸው ላይ ተጠርተው በአዳማ ከተማ በሥልጠና ላይ እንደሚገኙ አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው ሰልጣኞች አረጋግጠዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here