ሲያወዛግቡ የነበሩት ቋሚ ኮሚቴዎች ሰብሳቢ ተመረጠላቸው

0
584

የሁለት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችን አልቀበልም በማለት ሁለት ጊዜ ውድቅ በማድረጉ ሲያነጋግር የነበረው የተወካዮች ምክር ቤት አዳዲስ እጩዎችን ተቀበለ።
ምክር ቤቱ ኅዳር 13/2011 ባካሔደው 7ኛ መደበኛ ስብሰባው፣ ያልተሟሉ የምክር ቤቱን የቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበሮችን ሹመት በማፅቅ እልባት ሰጥቶታል።
የውሳኔ ሐሳቡን መርምሮ በአብላጫ ድምፅ ያፀደቀው ምክር ቤቱ፣ ተስፋዬ ዳባን የውጭ ግንኙነትና የሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ ለምለም ሐድጎን ደግሞ የገቢዎች፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አድርጎ መርጧል።
ምክር ቤቱ ለውጭ ግንኙነትና የሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢነት ሁለት ጊዜ ዕጩ ሆነው የቀረቡለትን የቀድሞው የመከላከያ ሚንስትር ሞቱማ መቃሳ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል። በተመሳሳይ ምክር ቤቱ ለገቢዎች፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢነት ሁለት ዕጩዎች ቀርበውለት የነበረ ቢሆንም ዕጩዎቹን ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here