አየር መንገዱ ስለሜቴክ አውሮፕላን የሚያውቀው ነገር የለም

0
639

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወልደ ገብረ ማሪያም ጠፍቶ ስለተገኘው አውሮፕላን የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ሐሙስ፣ ኅዳር 14 በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቀዋል። የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ ሜቴክ ከገዛቸው አውሮፕላኖች መካከል አንዱ የት እንዳለ እንደማይታወቅ መግለጹን ተከትሎ የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን አየር መንገድ ግቢ ውስጥ መገኘቱን መዘገባቸው ይታወሳል። ከአውሮፕላኑ መገኘት ዜና ጋር በተያያዘ አዲስ ማለዳ ለአየር መንገዱ ሥራ አስፈፃሚ ላቀረበችላቸው ጥያቄ ስለሜቴክ አውሮፕላኖች የሚያውቁት ምንም ነገር እንደሌለ ምላሽ ሰጥተዋል።
የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ብርሀኑ ፀጋዬ ቀደም ብለው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አውሮፕላኖቹን ሜቴክ በ11 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ከእስራኤል መገዛቱን ገልጸው፣ በግዢው መንግሥት ወደ 24 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ጉዳት እንደደረሰበበት አስታውቀው ነበር።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here