የበላይነህ ክንዴ ቢዝነስ ግሩፕ ፌቤላ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ሥራ ጀመረ

0
668

ሐሙስ ሰኔ 15 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በደብረ ብርሃን ከተማ የተገነባው የበላይነህ ክንዴ ቢዝነስ ግሩፕ ፌቤላ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ወደ ማምረት ሥራ መሸጋገሩ ተገልጿል።

ፋብሪካው በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ሚኒባስ፣ ሚድባስ እና የከተማ አውቶብስ ተሽከርካሪዎችን ማምረት መጀመሩ ነው የተነገረው፡፡ፋብሪካው እስካሁን ለ150 ዜጎች ቋሚ ለ100 ዜጎች ጊዜያዊ የሥራ እድል ተጠቃሚ መድረጉን የገለጹት፤ የበላይነህ ክንዴ ቢዝነስ ግሩፕ የፌቤላ የመኪና መገጣጠሚያ ኢንዱስትሪ ሥራ አስኪያጅ መሀመድ አህመድ፤ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባም ለ440 ዜጎች ቋሚ፣ ለ250 ለሚሆኑ ዜጎች ጊዜያዊ በአጠቃላይ ከ700 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል እንደሚፈጥር ጠቁመዋል፡፡

ፋብሪካው በመጀመሪያ ዙር 216 መኪኖችን ለመገጣጠም አቅዶ እየሰራ መሆኑን የገለጹት ሥራ አስኪያጁ፤ ከ20 ቀን በኋላ የሚገጣጥማቸውን በኤሌክትሪክና በነዳጅ የሚሰሩ መኪናዎች ለገበያ ማቅረብ እንደሚገምር ተናግረዋል፡፡

ፋብሪካው በቀን 4 በነዳጅና በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖችን መገጣጠም እንዲሚችልና፤ ጥሬ እቃውን ለጊዜው ከቻይና እና ከአውሮፓ በማምጣት እንደሚገጣጠሙም ገልጸዋል፡፡የኤሌክትሪክ መገጣጠሚያ ፋብሪካው 2 ቢሊየን ብር ወጪ እንደረደረገበትም ተነግሯል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here