የቀድሞ የሱዳን ፕሬዝዳንት ለዓለም ዐቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እንደሚሰጡ ተረጋገጠ

0
519

በሕዝባዊ ተቃውሞ ከስልጣን የተነሱት የቀድሞ የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አል-በሽር ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተላልፈው ሊሰጡ ነው። የ75 ዓመቱ የቀድሞ የሱዳን ፕሬዝዳንት አል-በሽር ለዓለም ዐቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተላልፈው ሊሰጡ እንደሆነ የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልመሃመድ ሐዶክ አረጋግጠዋል። የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አልበሽር በስልጣን ዘመናቸው በዳርፉር የሚገኙ እና ዘር ሐረጋቸው ከአረብ የማይመዘዙ ሦስት ጎሣዎች ላይ ከፍተኛ ዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽመዋል ሲል መክሰሱ የሚታወስ ነው። ይህንም ተከትሎ ከአስር ዓመታ በፊት የእስር ማዘዣ አውጥቶባቸው የነበረ ቢሆንም በቁጥጥር ስር ሳይውሉ ቆይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አል-በሽርን ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ) አሳልፈው ለመስጠት ያላቸዉ ፍላጎት በመጥቀስ “ተጎጂዎች ፍትህ እን ዲያገኙ የምናደርገውን ጥረት ምንም አይነት እንቅፋት ሊያቆመን አይችልም” ብለዋል። በእስር ላይ የሚገኙት አልበሽር ሱዳንን ለሦስት አስርት ዓመታት መምራት ችለው የነበረ ቢሆንም በባለፈው ዓመት የተነሳ ተቃውሞን ተከትሎ በባለፈው ሚያዚያ በወታደራዊ ኃይል ከስልጣን ሊነሱ ችለዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here