ሂጅራ ባንክ የተከፈለ ካፒታሉ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ እንደሆነ አስታወቀ

0
593

አዲስ በመቋቋም ላይ የሚገኘው እና ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ራዕይ አድርጎ የተነሳው ጂጅራ ባንክ ስራ ለመጀመር ከባለ አክስዮኖች የሰበሰበው ገንዘብ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑን አስታውቋል። የባንኩ ዋና ስራ አስኪያጅ ጅብሪል ኡስማን ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት ባንኩ 527 ሚሊዮን ብር በላይ  የተከፈለ ካፒታል እና 1 ነጥብ 04 ቢሊዮን ብር በላይ ደግሞ ተፈረመ ካፒታል ማስመዝገቡን አስታውቀዋል።

እንደ ዋና ስራ አስኪያጁ ገለጻ ባንኩ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን እና አስፈላጊውን የካፒታል መጠን ያሟላ እና ይሰበሰባል ተብሎ ከታሰበው በላይ የተሰበሰበ ቢሆንም የአክስዮብ ሽያጩን እስከ ኅዳር 15/2012 ድረስ ማራዘሙ ታውቋል። እንደ ምክንያት የተቀመተው ደግሞ በተለያዩ ምክንያት አክስዮን መግዛት ፈልገው ያልቻሉ ሰዎች ቅሬታቸውን በማሰማታቸው ጊዜ እንደተጨመረ ለማወቅ ተችሏል።

አንድ ሚሊዮን አክስዮኖችን ለገበያ ያቀረበው ባንኩ የአንድ አክስዮን ዋጋ 1 ሽሕ ብር እንደሆነ አስታውቋል። በጠቅላላውም የአንድ ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው አክስዮኖች እንዳሉት ዋና ስራ አስኪያጁ አስታውቀዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here