ኦነግ የአገር አቀፍ ፓርቲ ፍቃድ ከምርጫ ቦርድ አገኘ

0
686

የኦሮሚያ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2000 ፈቃድ መሰረት ከምርጫ ቦርድ ፈቃድ አገኘ። በዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ የፖለቲካ ፓርቲ የምዝገባና የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ትናንት ኅዳር 4 2012 የተሰጠው ሲሆን አገር አቀፍ ፓርቲ መሆኑ ተረጋግጧል።

 

ከዚህ ቀደም ለዓመታት በህዝብ ተወካዮች ሽብርተኛ ድርጅት ተብሎ ተሰይሞ የነበረው ኦነግ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐብይ አሕመድ ስልጣን ከያዙ በኋላ በአስመራ በተደረጉ ሦስት ድርድሮች በሰላማዊ መንገድ ወደ ሀገር ገብቶ ለመፎካከር መስማማቱ ይታወሳል። ከዚህ ቀደም በመረራ ጉዲና (ፕሮፌሰር) ከሚመራው የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ጋር ጥምረት ለመፍጠር ስምምነት ላይ ደርሶ እንደነበር ይታወሳል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here