የኢትዮጵያ አየር መንገድ 20ኛዉን የሼባ ማይልስ ምስረታ በዓል አከበረ

0
1360

ሼባ ማይልስ 20ኛ የምስረታ በዓሉን እና የደንበኞች ቀን ኅዳር 2/ 20112 በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል አከበረ። በበዓሉ ላይ የመንግሥት ሚኒስትሮች፤ አምባሳደሮች፤ የዲፕሎማት ቤተሰብ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በእለቱም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሼባ ማይልስ ፕላቲንየም የረዥም ጊዜ ደንበኞች ለሼባ ማይልስ ላሳዩት ታማኝ የደንበኝነት አስተዋፅዖ እና ድጋፍ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራ አስፈጻሚ ተወልደ ገ/መድኅን ዶክተር) በእለቱ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ባለፉት ዓመታት ለአየር መንገዱ አባሎቻችን አማራጭ አገልግሎቶችን ስናቀርብ በመቆየታችን ደስተኞች ነን ያሉ ሲሆን፣ የአየር መንገድ ደንበኞች ለአየር መንገዱ ዕድገት ትልቅ አሰተዋጽኦ በማበርከት ላይ ናቸው ብለዋል።
አየር መንገድ ለደንበኞች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ባለዉ ከፍተኛ ፍላጎት፣ የአየር መንገድ አባል ከሆኑ፤ ካልሆኑም እና ከሌሎች አጋሮች ጋራ በጋራ እየሠራ መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂዉም በመታገዝ ለደንበኞች የሚሰጠዉን አገልግሎቱን ለመጨመርም እየሠራ ነዉ ብለዋል።

በመጨረሻም ታማኝ ደንበኞቻቸው እና አጋሮቻቸው ላሳዩት ታማኝነት እና ለሥራው መሳካት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና ተበርክቶላቸዋል። ሼባ ማይልስ ሥሙን በጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ንግሥት ሰይሞ በይፋ ሥራ የጀመረዉ በፈረንጆቹ 1999 ነበር።

ቅጽ 2 ቁጥር 54 ህዳር 6 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here