በአራት ወራት ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ የገቢ ግብር ተሰበሰበ

0
302

የገቢዎች ሚኒስቴር በ2012 የበጀት ዓመት የአራት ወራት ክንውን ከባለፈው ዓመት የ21 ቢሊዮን ብር ብልጫ በማሳየት እና የእቅዱን 102 በመቶ በማሳካት 90 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

በበጀት አመቱ 248.3 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ያቀደው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንደ ባለፈው አመት ከግብር እዳ ያለመሰብሰቡን ይፋ ያደረጉት የገቢዎች ሚኒስቴሯ አዳነች አቤቤ ከ 6 ቢሊዮን ብር በላይ የግብር እዳ አለመሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡ ለገቢ አሰባሰቡ መሻሻል ዋነኛ ምክኒያት የሆነው የህግ ማስከበር ስራዎች ተጠናክረው መሰራታቸው እና በህቡእ ኢኮኖሚው ውስጥ በየሚዘዋወረውን ግንዘብ መቆጣጠር መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የውስብስብ ህጎች መጠን መቀነስ እና የቀሩትም ግልጽ እንዲሆኑ የማድረግ ስራዎች በዋናነት ለገቢ መሻሻሉ ከፍተኛ ድርሻ አለው ተብሏል፡፡ የቢሮክራሲ ማሻሻያ እና የሰራተኞች የስራ ላይ ቅልጥፍና መጨመር አንደ ምክኒያት ተወስዷል፡፡

በቀጣይም የግብር መሰረቱን ለማስፋት እና የሚታዩ የአገልግት አሰጣጥ ችግሮችን ለመቀነስ ይረዳል ሲሉ ሚኒስተሯ ለኤቢሲ ተናግረዋል፡፡ በ 2011 በስድስት ወር የተሰበሰበው ገቢ 86 ቢሊዮን ሲሆን በተያዘው አመት ግን በአራት ወራት ብቻ 90 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡ ከፍተኛ መሻሻል እንደሆነም ተገለጿል፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 54 ህዳር 6 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here