ሕገ መንግሥቱን በኀይል ለመናድ ሞክረዋል በተባሉ ግለሰቦች ላይ ክስ ሊመሰረት ነው

0
470

የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ማክሰኞ ኅዳር 2/ 2012 በሰተው መግለጫ ሕገ መንግሥቱን እና ሕገ መንግሥታዊ ስርአቱን ለመናድ በማሰብ መፈንቅለ መንግሥት ለማደረግ ሰኔ 15/ 2011 በብርጋዴል ጀኔራል አሳምነው ጽጌ የተመራ ነው በተባለ ድርጊት የተጠረጠሩ ከ 50 በላይ ግለሰቦች ላይ በቀጣዩ ሳምንት ክስ እንደሚመሰረት ታወቀ።

የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር እና የመከላከያ ሰራዊት ኤታማጆር ሹም ጨምሮ ፌደራል እና ክልል ከፍተኛ አመራሮችን ለማጥቃት በማሰብ ለሰባት ሳምንታት የስለላ እና የደህንነት ባለሞያዎች ሰልጥነው ነበር ሲሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ብርሃኑ ፀጋዬ ገልጸዋል።

‹‹የክትትል ሥልጠና፣ የመረጃ ትንተና እና አሰባሰብ፣ ስውር ጦርነት አስፈላጊነት እና መንገዶችን፣ የሥነ ልቦና እና ኢኮኖሚ ጦርነት›› የሚሉ የሥልጠና መንገዶችን በመለየት ስልጠና መሰጠቱን በማስረጃ መረጋገጡን ተናግረዋል። ይህም መፈንቅለ መንግሥቱ እንዲሳካ ምቹ ሁኔታን የመፍጠር ሒደት ነበር ያለው አቃቤ ሕግ፣ አክሎም የወታደራዊ፣ የአርሶ አደር እና የከተማ አደረጃጀትን ጨምሮ የተለያዩ ሰንሰለቶችን በመላው አገሪቱ በመዘረጋት ለወንጀል ድርጊት አሳትፈዋል ተብሏል።
‹‹በአጎራባች ክልልች በተፈጠሩ አለመረጋጋቶች የተነሱ ግጭቶችን መምራት እና የማስተባበር ድርጊት›› ሲሉ ብርሃኑ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። ‹‹ሕዝቡን እርስ ብርሱ በማጋጨት እና ለዋናው ዓላማ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ተሰርቷል›› ሲሉ የገለጹም ሲሆን በግለጽ የትኛውን ግጭት ማን እንደመራው እና እንዳስተባበረው ለማወቅ እንዳልተቻለ ግን ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ የተፈጸመው ድርጊትም በተለይ ሠራዊቱን ለማዳከም እና እርስ በእርሱ እንዲከፋፈል፤ ይህም በአማራ ክልል ሥልጣኑን በቀላሉ ለመቆጣጠር ነበርም ተብሏል። አክለውም ከሟች ጄኔራል ሰአረ መኮንን ባሻገር ሌሎች የመንግሥት ባለሥልጣናትም ዒላማ እንደነበሩ እና ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ አንዱ እንደነበሩ ‹‹ጄነራል ሰአረ ላይ በሚፈጸመው ጥቃት ወቅት ብርሃኑ ወደ ቦታው ስለሚያመሩ እርምጃ ለመውሰድ ታስቦ ሌላ ሰው ሲጠብቃቸው የነበር ቢሆንም ሳይመጡ በመቅረታቸው እርምጀ ሳወሰድባቸው ቀርቷል›› ብለዋል። ጄኔራል ሰአረ ላይ ግድያ የፈፀመው ግለሰብም መሳፍንት ጥጋበቡ የተባለ የግል ጠባቂ እንደሆነ ተናግረዋል።

የመንግሥት በጀት እና ከተለያዩ ባለሃብቶች የተሰበሰበ ገንዘብ ለዓላማው በተግባር ላይ መዋሉንም ብርሃኑ ገልፀዋል። ከቀጥታ ተሳታፊዎቸች ውጪም ጽንፈኛ አክቲቪስቶች ተሳትፈዋል ሲሉ ብርሃኑ ቢደመጡም፣ ስም ከመጥቀስ ግን ተቆጥበዋል።

በአጠቃላይ 277 ግለሰቦች በባህር ዳር እንዲሁም በአዲስ አበባ 140 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር እንደዋሉም በመግለጫው ተገልጿል። ባህር ዳር ላይ 45 ተጠርጣሪዎች የወንጀል ተሳትፎአቸው አነስተኛ በመሆኑ ወደ ምስክርነት እንዲቀየሩ ተደርጓል። ቀዳሚ ምርመራ በ 47 ተጠርጣሪዎች ላይ የተደረገ ሲሆን በአጠቃላይም 55 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ለመመስረት ዝግጅት ማገባደዱንም የጋራ የምርመራ ቡድኑ ገለጿል።

የወንጀሉ ዋና ዓላማ መንግሥት በኃይል በማስወገድ ሥልጣንን በኀይል ለመቆጣጠር የተደረገ ስለመሆኑ ድርጊቱን በታቀደ መልኩ የተፈጸመ ወንጀል እንደሆነ ገልጸዋል። ወንጀሉን በዋናነት የመሩት ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ፤ ሻምበል መማር ጌትነት፤ ሻምባል ታደሰ እሸቴ፤ ሻለቃ አዱኛ ወርቁ የተሳተፉት ስለመሆኑ ሌሎች ለዚህ ተግባር ተልዕኮ የተሰጣቸው በማሳተፍ የተፈጸመ ስለመሆኑ አቃቤ ሕግ በሰጠው መግለጫ አመላክቷል።

ጥቃቱ የክልሉ ፕሬዝንት ጽ/ቤት ፤ የፖሊስ መኮንኖችን በአዴፓ ጽሕፈት ቤት እንዲሁም በእንግዶች ማረፊያ ያነጣጠረ እንዲሆን የተደረገ ነበር ተብሏል። በጥቃቱ 15 ሰዎች ለሞት 20 የአካል ጉዳት እንዲሁም በርካታ የንብረት ውድመት ስለመድረሱ የምርመራ ውጤቱ ያስረዳል።

በባህር ዳር 39 ትዕዛዝ የወጣባቸው ተጠርጣሪዎች እስከ አሁን ያልተያዙ ስለመሆኑ በክትትል የሚገኝ ሲሆን፣ 22 ተጠርጣሪዎች የባንክ ሂሳብ ታግዶ እየተጣራ የሚገኝ፣ በባህር ዳር ጥቃት 147 የሰው ማስረጃ ቃል መቀበል የተቻለበት ስለመሆኑ ዋና አቃቤ ሕግ ብርሃኑ ገልጸዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 54 ህዳር 6 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here