በሶስት ቀናት ዉስጥ 487 ጥይትና 9 የቱርክ ሽጉጥ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ

0
960

ከህዳር 09 2012 ጀምሮ ባሉት ሶስት ቀናት በተለያዩ ጉምሩክ ጣቢያዎች በተደረገ ፍተሻ 487 ጥይትና 9 የቱርክ ሽጉጥ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ጉምሩክ ኮሚሽን በአዋሽ ጉምሩክ ኮሚሽን ፅህፈት ቤት አለበረከቴ በተባለ ቦታ በተደረገ ፍተሻ ከኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጋር ተቀላቅሎ ሊያልፍ የነበረ 218 ጥይት ፣ 126 የብሬን ጥይት 92 የክላሽ ጥይት ከአራት ተጠርጣሪዎች ጋር በሕዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ ውስጥ መያዙ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በሞያሌ ጉምሩክ በኩል በተደረገ ፍተሻ ዘጠኝ የቱርክ ሽጉጥ እና 96 ጥይት በሕዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ መቀመጫ ውስጥ ከኦሮ ኮንሶ ወደ ሞያሌ ሲገባ ተይዟል፡፡

በአጠቃላይም ከሕዳር 09 2012 ጀምሮ በተደረገ ፍተሻ 487 ጥይት እና 9 የቱርክ ሽጉጥ ለመያዝ መቻሉን ገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል። በተመሳሳይም በቦሌ ኤርፖርት የዓለም አቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በትናንትናው ዕለት የኤርትራ ዜግነት ያላቸው ኹለት ተጠርጣሪዎች 86 ሺህ 350 ዩሮ የምንዛሬ ዋጋው 2 ሚሊዮን 895 ሺህ 315 ብር እና 89 ሺህ 90 የስዊዝ ፍራንክ የምንዛሬ ዋጋው 2 ሚሊዮን 715 ሺህ 463 ብር ከአዲስ አበባ ወደ ውጭ ሀገር ሊያስወጡ ሲሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሚኒስቴር መ/ቤቱ ገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም 17.9 ኪ.ግ የሚመዝን የተሠራና ያልተሠራ የብር ጌጣጌጥ ግምታዊ ዋጋው 716 ሺህ ብር የሚሆን ከለበሱት የሰደርያ ጃኬት ውስጥ ሊያዝ ችሏል።
በአጠቃላይም 5 ሚሊዮን 610 ሺህ 778 የውጭ ሀገር ገንዘብና 716 ሺህ ብር የብር ጌጣጌጥ በድምሩም 6 ሚሊዮን 326 ሺህ 778 ብር በቁጥጥር ስር መዋሉን ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ቅጽ 2 ቁጥር 55 ኅዳር 13 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here