የግል ባንኮች ሲያበድሩ ከልማት ባንክ የሚገዙት ቦንድ እንዲቀር ተወሰነ

0
376

ብሔራዊ ባንክ የግል ባንኮች ባበደሩ ቁጥር የብድሩን 27 በመቶ በሚሆን ገንዘብ ቦንድ እንዲገዙ የሚገደዱበት አሰራር እንዲቆም ወሰነ፡፡
አዲስ በተዘጋጀው እና ከ 2011 ጀምሮ ለውጥ እንደሚደረግበት ሲነገር በነበረው አሰራር መሰረት የግል ባንኮች ባበደሩ ቁጥር ከብድሩ 27 በመቶ የሚመጣጠን ገንዘብን በማውጣት ከብሔራዊ ባንክ ቦንድን እንዲገዙ እንደማይገደዱ ተገልጿል ።

አዲሱ መመሪያ በሥራ ላይ መዋሉ በቀውስ ውስጥ ያለው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብድር የሚያቀርብበት ገንዘብ ስለሚቀንስ በመንግሥት በኩል አዲስ አይነት አማራጭ ሳይታሰብ እንዳልቀረ አመላካች ነው ።

የግል ባንኮች ከሚሰጡት ብድር ውስጥ 40 በመቶው የአጭር ጊዜ ፤ 40 በመቶው ደግሞ የመካከለኛና ቀሪው 20 በመቶ ደግሞ የረጅም ጊዜ ብድር እንዲሆን ታዘዋል ። አዲሱ አሠራር የግል ንግድ ባንኮች 20 በመቶ የረጅም ጊዜ ብድር እንዲሰጡ ከታዘዙ ባንኮች የረጅም ጊዜ ብድርን ለሚፈልጉ እንደ አምራች ኢንዱስትሪ ላሉ ዘርፎች በሰፊው ብድርን እንዲያቀርቡ ያስችላቸዋል ።

የግል ባንኮቹም የረጅም ጊዜ ብድር የመስጠት ሥራ ውስጥ የሚገቡ ከሆነ እንደከዚህ ቀደሙ በአጭር በአጭር ጊዜ ውስጥ ብድር እየሰጡ ቦንዱን የመግዛት አዝማሚያቸው ይቀንሳል ይህም በባንክ ኢንዱስትሪው ላይ ለመሰማራት ለሚፈልጉ መልካም አጋጣሚ እንደሚፈጥር ተገልጿል ።

በሌላ በኩል አዲሱ የብሔራዊ ባንክ መመሪያ ለተበዳሪዎች ከፍተኛ እፎይታን በሚሰጥ እና ብድር መመለሻ ጊዜቸውን በማራዘም ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 55 ኅዳር 13 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here