በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በደረሰ የትራፊክ አደጋዎች የ49 ሰዎች ሕይወት አለፈ

0
808

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እሁድ ኅዳር 14/2012 በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ49 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፋና ብሮድካስቲንግ ዘግቧል። አደጋዎቹ የደረሱት ከአዲስ አበባ ወደ አምቦ፣ ከመቱ ወደ አዲስ አበባ እና ከቢሾፍቱ ወደ አዳማ ከተማ ሲጓዙ በነበሩ ተሽከርካሪዎች መሆኑ ታውቋል።

አንዱ አደጋ የደረሰው ከአዲስ አበባ ወደ አምቦ 20 ሰዎችን አሳፍሮ የነበረ መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ በተለምዶ ሀይሩፍ በመባል የሚጠራ ተሽከርካሪ ከሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ በመጋጨቱ ሲሆን የ17 ሰዎች ቀጥፏል። ሌላኛው አደጋ የደረሰው ከመቱ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ኦዳ ባስ ገተማ ተብሎ በሚጠራ ከተማ አካባቢ በመገልበጡ ሲሆን በአደጋውም በተመሳሳይ የ17 ሰዎች ሕይወት ሊያልፍ ችሏል።

በተጨማሪ ከአዲሰ አበባ 99 ኪሎ ሜትር ርቀት ከምትገኘው አዳማ ወደ ቢሾፍቱ ሲያመራ የነበረ ተሽከርካሪ ላይ የትራፊክ አደጋ በመድረሱ 15 ሰዎች ሕይወታቸው ሊያልፍ ችሏል። በየዓመቱ ከ4000 በላይ ሰዎች በትራፊክ አደጋ የተነሳ ሕይወታቸው ያልፋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here