አሊባባ ግሩፕ ከኢትዮጵያ ጋር በኤሌክትሮኒክስ የታገዘ የንግድ ማዕከል ለመገንባት ተፈራረመ

0
352

በኢትዮጵያ አለም አቀፍ በኤሌክትሮኒክስ የታገዘ እና አለም አቀፍ የንግድ አጋርነት በኤሌክትኒክስ የሚያስተሳስር ማዕከልን ለመገናባት አሊባባ ግሩፕ ከኢትዮጵያ ጋር ተፈራረመ። eWTP የተባለው እና በቀጣይ እንደሚገነባ ስምምነት ላይ የተደረሰው ማዕከል አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን በማካተት ድንበር ተሸጋሪ ግብይቶችን በማዘመን የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣም ተገልጿል።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የአሊባባ ግሩፕ መስራች ጃክ ማ እና Ant የተባለው አለም አቀፍ ገንዘብ ተቋም ሊቀመንበር ኢሪክ ጂንግ በተገኙበት የመግባቢያ ሰነዱ ተፈርሟል። ኢትዮጵያ አዲሱን የቴክኖሎጂ የንግድ መገኛ ማዕከል ስታስገነባ ከአፍሪካ ከሩዋንዳ በመቀጠል ኹለተኛዋ አገር እንደምትሆን ተነግሯል። አዲሱ አጋርነት  በኢትዮጵያ ተግባራዊ የሚሆነው በእስያ ቻይና እና ማሌዥያ እንዲሁም በአውሮፓ ቤልጀም እና በአፍሪካ ደግሞ ሩዋንዳ ተግባራዊ ተደርጎ በኹለት ዓት ውስጥ እምርታ በማሳየቱ እንደሆ ተጠቅሷል። የማእከላቱ የሚደረገው የንግድ ግብይት ሲጨምር ነጋዴዎችም በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ የሚኖራቸው ዕድልም እንደሚሰፋ ተጠቁሟል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here