ኢንዱስትሪዎችን በቴክኖሎጂ መደገፍ የሚያስችል ስምምነት ተደረገ

0
377

የፌዴራል አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪ ማስፋፊያ ባለሥልጣን፣ የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ፤ የትምህርት ሥልጠና ኤጀንሲ ከአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት ጋር በመሆን በ21 የልኅቀት ማዕከላት አማካኝነት፤ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች የክህሎት ሥልጠናን በቴክኖሎጂ ለማበልፀግ የጋራ እቅድ ለማዘጋጀት ተስማምተዋል።

የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት በአዳማ ከተማ ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ እንደገለፀው፣ በፌዴራል ደረጃ ሦስቱ ተቋማት ለአነስተኛ እና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ውጤታማ ድጋፍ እንዲደረግ ተስማምተዋል።

ባለሥልጣኑ በጋራ ለመሥራት መስማማቱ፣ ተቋማቱ የሚሰጧቸውን ድጋፎችና አገልግሎቶች በማቀናጀት የኢንዱስትሪዎቹን ፍላጎት ያገናዘበ ውጤታማ ድጋፍ በጋራ ለመስጠት ያስችላል ተብሏል። ኢንዱስትሪዎችን በአስተሳሰብም ሆነ በአመለካከት ለውጥ እንዲያመጡ በማድረግ ወደተሻለ ደረጃ ማድረስም ወሳኝ መሆኑ ተጠቁሟል።
የጋራ እቅዱ የልህቀት ማዕከላት የኢንዱስትሪዎች ክህሎትንና የቴክኖሎጂ ሽግግርን እንዲያፋጥኑ፣ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ውጤታማ በሆነ አግባብ የሚሰጡበትን ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ መሆኑም ተገልፆል።

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ኢንዱስትሪዎች በተሰማሩበት ዘርፍ ደረጃውን የጠበቀ ገበያው የሚፈልገውን ምርት ማምረት እንዲችሉም አቅም መፍጠር ነው ተብሏል።

ቅጽ 2 ቁጥር 56 ኅዳር 20 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here