ዳሰሳ ዘ ማለዳ ኅዳር 29/2012

0
942

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለኅብረተሰቡ ያቀረበውን የድጎማ ማሻሻያ 5 ቢሊዮን ብር እንደማይከፍል አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ። (ፋና ብሮድካስቲንግ)
…………………………………………………………
በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የመንግስት ከፍተኛ የትምህረት ተቋማት በፌደራል ፖሊስ እንዲጠበቁ መወሰኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። (ቢቢሲ)
…………………………………………………………
የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ወደ ባንክ ከፍ ለማለት ሒደት ላይ መሆኑን አስታወቀ። ባንኩ ግብረ ሰናይ ድርጅት በማቋቋምም ማኅበራዊ ግልጋሎቶችን ለመስጠት ዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል። (አብመድ)
…………………………………………………………
በሴቶች የንጽሕና መጠበቂያ ምርቶች ላይ ተሰማራችው ፍሬወይኒ መብርሀቱ የሲኤንኤን 2019 የዓመቱ ጀግና በመባል አሸናፊ ሆናለች። ፍሬወይኒ የአንድ መቶ ሽሕ ዶላር ሽልማትም ይበረከትላታል።(አዲስ ማለዳ)
…………………………………………………………
በአዲስ አበባ በሳለፍነው የእረፍት ቀናት ባጋጠሙ ኹለት የእሳት አደጋዎች ከ400 ሽህ ብር በላይ እንደወደመ አዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። (ኢትዮ ኤፍ ኤም)
…………………………………………………………
በሳዑዲ ዐረቢያ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር አህመድ አል ቃጣን የሚመራውና ሃምሳ አባላት ያሉት የሳዑዲ ዐረቢያ የመንግስትና የንግድ ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ የሦስት ቀናት የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል። (ዋልታ)
…………………………………………………………
የኢትዮጵያ ፣ ሱዳንና ግብጽ የውሃ ሚንስትሮች የሦስትዮሽ ውይይት በአሜሪካ ዋና ከተማ ዋሽንግተን እየተካሔደ ነው። ከኢትዮጵያም ወገን ወደ ዋሽንግተን ያቀናው ልዑክ በውጭ ጉዳይ ሚንስትር ገዱ አንዳርጋቸው የተመራ ነበር። (አዲስ ማለዳ)
…………………………………………………………
ከአበረታች ንጥረ ነገሮች ጋር በተያያዘ የዓለም አቀፉ ፀረ አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ ሩሲያን ለአራት ዓመታት ከማንኛውም ስፖርት ማገዱን አስታወቀ። (ፋና ብሮድካስቲንግ)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here