የኢትዮጵያ ፣ሱዳንና ግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ስብሰባ ተጠናቀቀ

0
804

በአሜሪካ ዋሽንግተን ሲካሔድ የቆየው የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ስብሰባ ተጠናቋል። በኅዳሴው ግድብ ዙሪያ ሲመክር የቆየው የሦስቱ አገራት የሚንስትሮች ስብሰባ በውሃ ሚንስትሮች ደረጃ የተካሔዱትን የባለሙያዎች ስብሰባ ያመጡትን ለውጦች ተመልክቷል።

በቀጣይ የሚካሄዱ መሰል ኹለት ስብሰባዎችም በግደቡ የውሃ አሞላል እና አስተዳደር ላይ ህግና መመሪያ እንዲያዘጋጅ፣ የድርቅ ሁኔታዎች ተብለው የሚወሰዱትን እና ድርቅን ለመከላከል የሚወሰዱ እርምጃዎችንም ከወዲሁ ለማስቀመጥ ተስማምተዋል።  የሦስቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች በተሳተፉበት ስበሰባ ላይ የውሃ ሚንስትሮችም የተሳተፉ ሲሆን የአሜሪካ መንግሥት እና የዓለም ባንክ ተወካዮችም ተገኝተዋል።

በኅዳሴው ግድብ የውሃ አሞላል እና አስተዳደር በተመለከተ የሚዘጋጁ የቴክኒክ ሕጎችና መመሪያዎች በኢትዮጵያ እንደሚፈፀም የታወቀ ሲሆን ወቅታዊ የአየር ሁኔታን ታሳቢ በማድረግ ሦስቱ አገራት በመነጋገር ሕጉን ሊያሻሽሉ እንደሚችሉ ተገልጿል።

የሦስቱ አገራት ሚንስትሮች የሚደረሰውን ስምምነት ለማጠናቀቅ ፣ በካርቱምና በአዲስ አበባ የተደረጉትን ስብሰባዎችን ውጤትም ለመገምገም በፈረንጆቹ ቀጣይ ዓመት ጥር 13/2020 በዋሽንግተን ደግመው እንደሚገኙ ታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here