ዳሰሳ ዘማለዳ ኅዳር 30/2012

0
746

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ በኖርዌይ ኦስሎ በተዘጋጀ ደማቅ ዝግጅት የኖቤል ሽማታቸውን ተቀብለዋል። በሽልማት ስነ ስርዓቱ ላይ በርካታ ታዋቂ ግለሰቦችና ቀድሞ የኖቤል ሽልማት አሸናፊዎች ተገኝተዋል።(አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………………………..

የትግራይ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ በሚል በአማርኛ የሚታወቀው እና  በትግርኛ ምህፃሩ ዴምህት ራሱን አክስሞ ከህወሓት ጋር በመዋሃድ ለመታገል መወሰኑን አስታወቀ፡፡ የትግራይ ክልል ገዢ ፓርቲ ህወሓት በበኩሉ የዴምህትን ውሳኔ አድንቋል፡፡ (ዶቼ ቬለ)

…………………………………………………………………………….

‹የአማራ ገበሬዎች ቡና አምራች ኅብረት ሥራ ማኅበር ዩኒዬን› በ2012 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ  ዓመት 180 ኩንታል ቡና ወደ ጀርመን በመላክ በውጭ ንግድ ላይ ተሳትፎ ማድረጉ ተገለጸ፡፡ (አብመድ)

……………………………………………………………………………

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ልዋሃድ እችላለሁ  ሲል አስታወቀ። ፓርቲው የምስረታ ጉባኤውን ኅዳር 27 እና 28/2012  በማካሔድ ስያሜውንም ከትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ወደ ትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መቀየሩን አስታውቋል፡፡ (ኢትዮ ኤፍ ኤም)

…………………………………………………………………………….

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለወላይታ ህዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄ በአጭር ጊዜ ውስጥ ምላሸ ካልሰጠው ጉዳዩን በአቤቱታነት ወደ ፌዴሬሸን ምክር ቤት እንዲወሰድ የቀረበለትን አጀንዳ የወላይታ ዞን ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ አፀደቀ:: (ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን)

…………………………………………………..

በአዲስ አበባ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ሴት ተማሪዎች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እንዲሰራጩ በሚያስችልበት ሁኔታዎች ዙሪያ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በጉዳዩ ላይ ከሚሰሩ የበጎ ፍቃድ ማኅበራት ጋር ተነጋገሩ፡፡ (አዲስ ማለዳ)

…………………………………………………………………………….

በቅማንትና አማራ ሕዝቦች መካከል የነበረውን መልካም ግንኙነት ለመመለስ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እየተደረገ መሆኑን የአማራ ክልላዊ መንግስት ኮሚንኬሽን አስታወቀ። (አብመድ)

…………………………………………………………………………………….

በየመንገዱ የስልክ ስክሪን ማጠንከሪያ ተብሎ አገልግሎት ላይ እየዋለ ስላለው ፈሳሽ የሚያውቀው ነገር አለመኖሩን የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለሥልጣን አስታወቀ። ናኖ ቴክኖሎጂ በውስጡ በርካታ ነገሮችን እንደሚይዝና ጠንከር ያለ ምርመራ የሚያስፈልገው ነገር እንደሆነም ባለስልጣኑ አስታውቋል። (ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here