በወለጋ ዩኒቨርስቲ በሦስት ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለፀ

0
904

በወለጋ ዩኒቨርስቲ ትናንት ኅዳር 30/2012 እና ዛሬ ማለዳ ታኅሳስ 1/2012 በሦስት ዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው በትናንትናው ዕለት በወለጋ ዩኒቨርስቲ በኹለት ተማሪዎች ላይ ጉዳት ደረሰ ሲሆን ዛሬ ማለዳ ላይም በአንድ ተማሪ ላይ ጉዳ መድረሱን አስታውቋል።

ጉዳት ለደረሰባቸው ተማሪዎች ተገቢውን የሕክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸው ሲሆን፤ ጉዳት አድራሽ ናቸው ተብለው የተጠረተሩ ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር እየዋሉ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በተለያዩ ቀናት በጎንደር ዩኒቨርስቲ ውስጥ አመጽ እና ብጥብጥ ለማስነሳት የሞከሩ እንዲሁም በአንድ ተማሪ ላይ ጉዳት በማድረስ ለህልፈት የዳረጉ ግለሰቦች ላይ ክስ የመመስረት ሑደት መጠናቀቁን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here