ከ7.7 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃና ዶላር መያዙ ታወቀ

0
770

በጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኅዳር 30/2012  ምሽት 3 ሰዓት ከብር 7ነጥብ 7 ሚሊዬን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ የገቢዎች ሚንስቴር እንዳስታወቀው  በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ኢት 45074/14652 ኮንቴነር የጫነ ተሽከርካሪ ሀሰተኛ ሰነድ በመያዝ ወደ አዲስ አበባ በመጓጓዝ ላይ እያለ ደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ ሀርቡ ከተማ ላይ በክልሉ ፖሊስ አባላት እና በጉምሩክ ሰራተኞች ትብብር ሊያዝ ችሏል፡፡

በቁጥጥር ስር የዋሉት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ‹‹40 ጫማ›› መጠን ባለው ኮንቴነር ተጭነው የነበረ ሲሆን ብር 5.6 ሚሊዬን ግምታዊ ዋጋ ያላቸው መድሃኒቶች እና ብር 2,184,000 ግምታዊ ዋጋ ያለው ልባሽ ጨርቅ በድምሩ ብር 7,784,000 ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች እንደሆኑ ከገቢዎች ሚንስቴር የተገነው መረጃ ያመለክታል።
በተመሳሳይ ዜና በቀን 30/03/2012 መሀመድ አብዱላሂ አብዲ የተባለ ግለሰብ በህገወጥ መንገድ ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጲያ 26,400 የአሜሪካን ዶላር /ሀያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ዶላር/በኢትዮጵያ ብር ዛሬ በዋለዉ የምንዛሪ ዋጋ 828,960 ብር/ ደብቆ ለማስገባት ሲሞክሩ በድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በደወሌ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ሰራተኞች ተይዟል፡፡ገንዘቡም ወደ ባንክ ገቢ የተደረገ ሲሆን ግለሰቡ ላይ በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ድሬዳዋ ዲቪዥን ተላልፎ ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here