ከ 30 ሺሕ በላይ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ ሊደረግ ነው

0
347

ዩዝ ኮኔክት ኢትዮጵያ የተሰኘ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ ሥራዎች ላይ በስፋት እንዲሳተፉ ለማድረግ የሚያስችል ፕሮግራም በኢትዮጵያ ሊተገበር ነው።

ፕሮግራሙን የኢፌዴሪ ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም እና ከአፍሪካ የአመራር ጥናት ማእከል ጋር በመተባበር የሚከናወን ሲሆን፣ ከ30 ሺሕ በላይ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ መንገድ እንደሚያመቻች ተገልጿል።

በዩኒቨርሲቲዎችና በመላው አገሪቱ ለሚገኙ በ 10 ሺዎች ለሚቆጠሩ ወጣቶች በዓመት 3 የቪድዮ ውይይት በማድረግ፣ እርስ በእርስ እንዲግባቡ እድል መፍጠር እንዲሁም 50 የወጣት ማእከላትን በማደስና ቁሳቁስ በማሟላት የሥራ ፈጠራና የሙያ ማበልጸግያ አገልግሎት እንዲሰጡ እንደሚደረግም መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል።

ፕሮግራሙ በአገራችን ሊያሳካ ካለማቸው ግቦች መካከልም ለ 30 ሺሕ ወጣቶች ብሔራዊ አገልግሎት ለማኅበረሰብ ለውጥ ያለውን ፋይዳ ማስገንዘብና በበጎ ፈቃድ ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ እንደሆነ ተገልጿል። በበጎ ፈቃድ ሥራውም አንድ ሚሊዮን ችግኞችን መትከል፣ 100 የአረጋውያንና የአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ፣ 50ሺሕ ዩኒት ደም እንዲለገስ በማድረግ መንግሥት ሊያወጣው የነበረውን 50 ሚሊዮን ብር ለማዳን እንደሚሠራ ተገልጿል።

ቅጽ 2 ቁጥር 58 ታኅሣሥ 4 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here