ለ16 ቀናት ሲከበር የነበረው ፀረ ፆታዊ ጥቃት ንቅናቄ ተጠናቀቀ

0
439

በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ለማቆም እና በሴቶች ላይ የሚደርሱ ሥነ ልቦናዊ እና አካላዊ ጫናን ለማቆም በእየ ዓመቱ የሚከበረው የፀረ ፆታዊ ጥቃት ንቅናቄ የ2012 መርሃ ግብር ተጠናቀቀ።
በኢትዮጵያ ለአስራ አራተኛ ጊዜ የተከበረው ንቅናቄው በተለያዩ በሴቶች ጥቃት ዙሪይ በሚሠሩ ማኅበራት እና ተቋማት በርካታ የመወያያ መድረኮችን በማዘጋጀት፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ተማሪዎች የተቋቋመዉ ‹ቢጫ ንቅናቄ› የተሰኘ ማኅበር በተለያዩ መርሃ ግብራት ሲከበር መቆየቱ ተገልጿል።
ማጠቃለያው እንዳለፉት ዓመታት በግቢ ዉስጥ በፀጥታ ደኅንነት ምክንያት ባይከበርም፣ ከተባበሩት መንግሥታት ሴቶች እና አዉስትራሊያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ይህን ዓለማቀፍ ዘመቻ፣ ‹‹የሠለጠነ ትዉልድ አስገድዶ መድፈርን ይፀየፋል›› በሚል በዓመቱ መሪ ሐሳብ ከማኅበራዊ ሚዲያ በተጨማሪ ኅብረተሰቡን አሳታፊ የሆኑ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት መልእክቶች ሲተላለፉበትና ጥሪ ሲቀርብበት ቆይቷል።
16 ቀን ፀረ ፆታዊ ጥቃት ንቅናቄ በ1977 በዓለማቀፍ የሴቶች አመራር ተቋም (Womens Global Leadership Institute) የተመሠረት፣ በሴቶች ላይ የሚደርስን ጥቃት ለማስቆም የተደራጀ እንቅስቃሴ ሲሆን፣ በዓለማቀፍ ደረጃ ከኅዳር 15 እስከ ኅዳር 30 የሚደረግ ዘመቻ ነው።

ቅጽ 2 ቁጥር 58 ታኅሣሥ 4 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here