10ቱ በርካታ የኖቤል ተሸላሚ ሰዎች ያሉባቸው አገራት

0
758

በስዊድናዊው ሳይንቲስት አልፍሬድ ኖቤል ኑዛዜ መሠረት በአውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1901 ጀምሮ ሲካሔድ 100 ዓመት በላይ አስቆጥሯል፤ የኖቤል ሽልማት። በስድስት ዘርፎች ማለትም በሰላም፣ በፊዚክስ፣ በኬሚስትሪ፣ በሥነ ጽሑፍ፣ በኢኮኖሚ፣ በሕክምና የሚሰጠው ሽልማቱ፣ ዳጎስ ካለ ስጦታው በተጨማሪ የዓለም ሎሬትነት ክብርም ይሰጥበታል።
የኖቤል ሽልማት ድረ ገጽ ተሸላሚ ግለሰቦችንና ተቋማትን በየራሳቸው እንጂ በሚገኙበት አገር ዘርዝሮ ያስቀመጠ ባይሆንም፤ ጃግራንጆሽ የተባለ ድረገጽ በርካታ ሎሬቶች ያሉባቸው ወይም ብዙ የኖቤል ተሸላሚዎች የሚገኙባቸውን አገራት ዘርዝሯል። ከእነዚህም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተሸላሚ የሚገኘው አሜሪካ ሲሆን፣ ብሪታንያ በኹለተኛ ደረጃ ላይ በ132 የኖቤል ተሸላሚዎች ተቀምጣለች። ኔዘርላንድ እና ጣልያን ደግሞ በ21 እና 20 ከ10ቱ ቀጥለው በተከታታይ የሚገኙ አገራት ናቸው።
ይህ ታድያ የሰላም ሽልማት ብቻ ሳይሆን በሌሎች አምስት ዘርፎች ጭምር እንደሆነ ልብ ይሏል! በአፍሪካ ደግሞ ዐስር አገራት ይህን የኖቤል ሽልማት በግል እንዲሁም ተጋርተው ማግኘት የቻሉ ሲሆን፣ ይህን ዝርዝር ኢትዮጵያ አሁን ላይ በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኩል መቀላቀል ችላለች።
እስከ አሁን በድምሩ 597 የኖቤል ሽልማቶች የተሰጡ ሲሆን፣ 950 ሎሬቶች ተሰይመዋል። ከእነዚህ 53 ሴቶች ናቸው፤ 24 ደግሞ ተቋማት። እንደ የሱፍ ማላላ ዓይነት በልጅነት እድሜ ሽልማቱን የተቀበሉ 17 ልጆች ሲኖሩ፣ በእድሜ አንጋፋ የሆኑ 97 ሰዎች የኖቤል ሽልማትን ማግኘት ችለዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 58 ታኅሣሥ 4 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here