በ 230 ሚሊዮን ብር የተገነባ የታሸገውሃ ፋብሪካ ወደ ሥራ ሊገባ ነው

0
638

‹ጤና› የተሰኘ በሰዓት 15 ሺሕ ሊትር የታሸገ የተፈጥሮ ማዕድን ውሃ ማምረት የሚችል ፋብሪካ ተገንብቶ ወደ ሥራ ሊገባ መሆኑ ተገለፀ።
የታሸገ የተፈጥሮ ማዕድን ውኃ ማምረቻ ፋብሪካው፣ በሀድያ ዞን ሶሮ ወረዳ ባምቦ ቀበሌ የተገነባ ሲሆን፣ ሀድያ የደረቅ ትራንስፖርት አገልግሎት የተሰኘ የአገር ውስጥ አልሚ ከ230 ሚሊዮን ብር ወጪ እንዳስገነባው ተገልጿል። ግንባታውን ለማጠናቅቅ ሦስት ዓመታትን ወስዷል።
የፋብሪካው ተከላ ተጠናቅቆ ታኅሳስ 11/2012 በይፋ ወደ ሥራ የሚገባ ሲሆንሥ በምርቀት ስነ ስርዓቱ ላይ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርዕሰቱ ይርዳው እና የዞኑ አስተዳዳሪዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል።
ፋብሪካው በ 30 ሺሕ ሜትር ስኴር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን፣ የሚያመርታቸው የውሃ ምርቶች ከ350 ሚሊ ሊትር እስከ ኹለት ሊትር ይዘት ያላቸው እንደሚሆኑ ተጠቅሷል። ለ 400 ቋሚ እና ለ 1500 ሰዎች ጊዜያዊ የሥራ ዕድል የሚፈጥርም ነው።
ዓለማቀፋዊ የጥራት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በማምረት ወደ ውጪ አገራት የመላክ ሐሳብ መኖሩ የተገለጸ ሲሆን፣ ከተለመደው የማከፋፈል ዘዴ በተጨማሪ ምርቶቹን በድረ ገጽ ገበያ ለማከፋፈል ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል ተብሏል።
በአካባቢውም ለፋብሪካው እና በአካባቢው ለሚኖር ኅብረተሰብ አገልግሎት መስጠት የሚችል የ16 ኪሎ ሜትር የመንገድ ጥርጊያ መከናወኑ እና የፋብሪካው ምርት ከሆነው አንድ ሌትር ውሃ ሽያጭ ላይ 0.2 ሳንቲም ወላጆቻቸውን ላጡ ሕፃናት እንደሚለገስ ተገልጿል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here