ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ክስ ተመሠረተባቸው

0
628

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የደን ምንጠራ ጋር በተያያዘ በተፈጠሩ የአሠራር ክፍተቶች ክስ እንደተመሠረተባቸው ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው፣ በኢንጅነር አዜብ አስናቀ ላይ የተመሠረተው ክስ ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ ላይ በተደረገ የደን ምንጠራ ጋር በተያያዘ የአሰራር ክፍተቶች መኖራቸውን ተከትሎ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። በ2010 ነሐሴ ላይ ከኃላፊነታቸው የተነሱት አዜብ፣ በተከሰሱበት መዝገብ የቀድሞ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ኮሎኔል ሙሉ ወልደ ገብርኤልን ጨምሮ 50 ሰዎች ይገኙበታል።

ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ወደ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚነት ከመምጣታቸው በፊት፣ የግልገል ጊቤ ሦስት የውሀ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል። 10 ዓመት የወሰደውና በ1.5 ቢለዮን ዪሮ ወጪ ሲገነባ የነበረው የግልገል ጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ አብዛኛው የግንባታ ክፍል ሳይጠናቀቅ፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የኤሌክትሪክ ኃይልና የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተብሎ ለኹለት ሲከፈል፣ የኃይሉን ዘርፍ በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ለመምራት በ 2006 መሾማቸው የሚታወስ ነው።

ቅጽ 2 ቁጥር 60 ታኅሣሥ 18 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here