በኹለት ወር ውስጥ አንድ ነጥብ ኹለት ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ንብረት ተወገደ

0
649

የመንግሥት ግዢ እና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በታኅሳስ እና በኅዳር 2012 ውስጥ ባወጣቸዉ ጨረታዎች ከ12 የመንግሥት ተቋማት የማይፈለጉ ንብረቶችን በማስወገድ አንድ ነጥብ ኹለት ሚሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።

በታኅሳስ ወር 2012 ኹለት ጊዜ ንብረት ሲወገድ፣ አንደኛዉ ከጂማ ዩኒቨርሲቲ 161 ያገለገሉ ንብረቶች ጨረታ ወጥቶ፣ 48 ከሚሆኑ ድርጅቶች ዘጠኙ ሰነድ አስገብተዋል። ከ161 ያገለገሉ ንብረቶች መካከል 108ቱ ሽያጭ ተፈፅሞ 570 ሺሕ ብር የሚጠጋ ገንዘብ ገቢ አድርጓል።

ኹለተኛ ደግሞ ከተለያዩ 11 የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የተውጣጡ 33 ያረጁ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ተፈፅሟል። በጨረታው ላይ 217 ተጫራጮች ሰነዶችን በመግዛት ተሳትፈዋል የተባለ ሲሆን፣ ከ33 መኪኖች መካከልም 22 ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ተፈፅሞ ወደ 7.1 ሚሊዮን ብር ገቢ ተደርጓል።

በአጠቃላይ አገልግሎቱ በታኅሳስ ወር 7.75 ሚሊዮን ብር ለመንግሥት ገቢ ማድረጉን አስታውቋል። በአጠቃላይ ከኅዳር ወር ጋር ተደምሮ 1.3 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ዋጋ ያለው ንብረት እንደተወገደ የግዢ እና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ መልካሙ ደፋሊ ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 60 ታኅሣሥ 18 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here