የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ያስገነባውን የመድኃኒት ማቀዝቀዣ መጋዝን አስመረቀ

0
645

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የተለያዩ መድኃኒቶችን ሳይበላሹ ማቆየት የሚችሉ ማቀዝቀዣ መጋዘኖችን በመገንባት አስመረቀ።

የመድኃኒት ማቀዝቀዣ ሰንሰለቱ ለፖሊዮ ክትባትና ለካንሰር የሚሆኑ መድኃኒቶችን ሳይበላሹ ለረጅም ጊዜ የማቆየት አቅም እንዳለውም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ዋና ዋና የጤና ችግሮች ላይ ያተኮሩ መሠረታዊ መድኃኒቶችና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎችን በመላ አገሪቷ ለሚገኙ ጤና ተቋማት የማቅረብ ሥራን በመሥራት ላይ ይገኛል። በዚህም ከ1 ሺሕ 300 በላይ መድኃኒቶችንና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎችን ደኅንነታቸውን እና ጥራታቸውን በማረጋገጥ ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ላይ መሆኑ ተገልጿል።

በመደበኛና በበጀት የሚቀርቡ 444 መድኃኒቶች፣ 178 የላብራቶሪ ሬጀንቶችን፣ 205 የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች በአጠቃላይ 1 ሺሕ 373 በዓይነት መሆናቸውን ኤጀንሲው ገልጿል።

ኤጀንሲው የሚያቀርባቸው የሕክምና ግብአቶች ደኅንነታቸውን ጠብቀው ለተጠቃሚው እንዲደርሱ በቂ ማቀዝቀዣ ያስፈልጋቸዋል የተባለ ሲሆን፣ አሁን የተመረጡ ክፍሎችም በተለይም እንደ ክትባት፣ ኢንሱሊን፣ የላብራቶሪ ሬጀንቶች እና ሌሎች የሕክምና ግብአቶችን ለማከማቸት የሚያገለግል የቅዝቃዜ ሰንሰለት የተገጠመላቸው መጋዝኖች ናቸው።

ቅጽ 2 ቁጥር 61 ታኅሣሥ 25 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here