በፓዊ ወረዳ ለወጣቶች ከተሰጠ 4.4 ሚሊዮን ብድር የተመለሰው 116 ሺሕ ብር ነው

0
462

በአማራ ክልል በመተከል ዞን በፓዊ ወረዳ ለወጣቶች የሥራ እድል ፈጠራ ከተሰራጨው 4.4 ሚሊዮን ብር ብድር ውስጥ የተመለሰው 116 ሺሕ ብር ብቻ መሆኑን የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች፣ ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ።

በዞኑ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች በወጣቶች ስፖርትና የሥራ ፈጠራ፣ በሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የመስክ ጉብኝት ያደረገው ኮሚቴው፣ በምልከታውም ወጣቶች በተለያዩ ኢንተርፕራይዞች ተደራጅተው፣ የሥራ እድል ተፈጥሮላቸውና ብድር ተመቻችቶላቸው በመኪና እጥበት፣ በባጃጅ ሥራ፣ በጫኝና አውራጅነት፣ በማዕድን በአሽዋና ድንጋይ ማውጣት ሥራ ተሰማርተው እየሠሩ መሆናቸውን ቋሚ ኮሚቴው ተመልክቷል።

በዞኑ ወረዳዎች የወጣቶች ጉዳይ ግብረ ኃይል በማቋቋምና ወጣቶችን በማደራጀት የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ቋሚ ኮሚቴው በጥንካሬ የተመለከተው ሲሆን፣ የብድር አመላለሱ ግን ዝቅተኛ እና በትኩረት ሊታይ የሚገባው መሆኑን አሳስቧል። ይሁን እንጂ በወረዳው ካለው 1 ሺሕ 439 የሥራ አጥ ወጣት ቁጥር አንጻር የሥራ እድል ፈጠራ አፈጻጸሙ ዝቅተኛ መሆኑን ገልጿል።

በተመሳሳይም ቡድኑ በማንዱራ ወረዳ የወጣቶች ስፖርት እንቅስቃሴን አስመልክቶ ባካሄደው የመስክ ምልከታ፣ በወረዳ ደረጃ 5 የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክቶች በእድሜ እርከን ተከፋፍለው በተለያዩ የስፖርት አይነቶች እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆናቸውን፣ በደረጃ ለ 13 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች የይዞታ ማረጋገጫ እንዲያገኙ መደረጉን የወረዳው የሥራ ኀላፊዎች ለቋሚ ኮሚቴው አብራርተዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 61 ታኅሣሥ 25 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here