ተስፋዬ ጌትነት የተባሉ የቀድሞ የካፒታል ጋዜጣ ጋዜጠኛ፣ የቀድሞ ቀጣሪያቸው የአሠሪ እና ሠራተኛ አዋጁን በመጣስ ደሞዝ፣ ጥቅማ ጥቅም እና ባገለገሉበት ቋንቋ የሥራ ልምድ ክልክሎኛል ሲሉ በቦሌ ክፍለ ከተማ የሥራ ክርክር ችሎች አርብ ታኅሳስ 24/2012 ክስ መሠረቱ።
ከሚያዚያ 2006 ጀምሮ በድርጅቱ ውስጥ በዘጋቢነት ሲያገለግሉ መቆየታቸውን በክሳቸው ውስጥ ያመላከቱት ተስፋዬ፣ በሕጉ መሰረት የአንድ ወር ማስጠንቀቂያ በመስጠት ድርጅቱን ለቀው ቢወጡም ድርጅቱ ግን አስፈላጊውን ክፍያ ሕጉ በሚያዘው መሰረት ሳይከፍላቸው ቀርቷል።
እንዲሁም ድርጅቱ ሊከፍላቸው የሚገባውን የአገልግሎት ክፍያም አንዳልከፈላቸው እና ፍርድ ቤቱም ይህንን እንዲያስፈፅምላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል።
ክሱን ከመመሥረታቸው በፊት በሕጉ መሰረት ቅድመ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን እና ተከሳሽ ግን ይህንን ባለመቀበላቸው ክስ መመስረታቸውን ተናግረዋል።
ጋዜጠኛው በአጠቃላይ የተለያዩ ክፍያዎች ተደምረው፣ 67 ሺሕ 200 ብር እንዲከፈላቸው እና ለሕግ ሂደቱ ያወጡትን ሦስት ሺሕ ብር ድርጅቱ እንዲከፍላቸው ፍርድ ቤቱ እንዲፈርድላቸው ጠይቀዋል።
ቅጽ 2 ቁጥር 61 ታኅሣሥ 25 2012



