በምርት ገበያ መቀመጫ በ3.2 ሚ. ብር ተሸጠ

0
431

በኢትዮጵያ ምርት ገበያ አንድ የአባልነት መቀመጫ በ3 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ብር በጨረታ ተሸጠ። ምርት ገበያ ሥራውን በጀመረበት ወቅት አንድ የአባልነት መቀመጫን በ50,000 ብር ይሸጥ ነበር።
ከአባላት በቀረበ ጥያቄ ሦስት የመደበኛ አባልነት መቀመጫዎችን ለመሸጥ ለስድስተኛ ጊዜ ጨረታ ያወጣው ምርት ገበያው ሦስት ተጫራቾችን በጨረታ አሳትፏል።
በጨረታው የቀረበው ከፍተኛው ዋጋ 3 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ሲሆን ዝቅተኛው ደግሞ 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ነው።
ከ10 ዓመታት በፊት የተመሠረተው ምርት ገበያው በ100 መሥራች አባላትና በ600 ደንበኞች ግብይት የጀመረ ሲሆን፤ አሁን 347 አባላት ሲኖሩት፥ ሁለት ዓይነት የአባልነት መደቦች አሉት። ተገበያይ አባል የሚገበያየው በራሱ ሥም ሲሆን፥ አገናኝ አባል ደግሞ በራሱ ወይም በደንበኞች ሥም መገበያየት የሚያስችል የአባልነት ዓይነት ነው።

ቅጽ 1 ቁጥር 3 ኅዳር 22 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here