በቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አመራሮች ላይ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ

0
463
በቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በታሰሩ አመራሮች በጌታቸዉ ወድሻ (ዶ/ር) እና በጌታሁን መርጋ ላይ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ መፍቀዱ ተገለፀ። አመራሮቹን ፍርድ ቤት ያቀረባቸዉ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መሆኑንና የቤንሻንጉል ክልል ምክር ቤት የፋይናንስና ገንዘብ ቋሚ ሰብሳቢ በነበሩት በአብደላሂ ሀጂ ግድያ እጃችሁ አለበት በሚል ክስ እንደሆነ የፓርቲዉ የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ ዩሐንስ ተሰማ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። በተጨማሪም የፓርቲዉ ሊቀመንበር የሆኑት አመንቴ ገሽ፣ ከአዲስ አበባ ተይዘዉ ወደ አሶሳ መወሰዳቸውንም ዩሐንስ አክለዉ ገልፀዋል። የክልሉ ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጥያቄውን ለክልሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጥር 1/ 2012 የ14 ቀናት የምርመራ ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ፣ የምርመራ ጊዜው የጠየቀው የምርመራ ቀን ሙሉ መፈቀዱ ተገልጿል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፓርቲው የቦርድን መመሪያ በመከተል የምስረታ ሂደት እያከናወነ መሆኑን እና አስፈላጊዉን መስፈርት ማሟላቱን የሚገልፅ እና የሚመለከታቸው ሁሉ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ደብዳቤ መጻፉን ዩሐንስ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። ክልሉ ፓርቲው በመጭዉ ምርጫ ጠንካራ ሆኖ እንዳይቀርብ ተፅዕኖ እያደረገባቸዉ እንደሆነና በክልሉ  ዴሞክራሲያዊ ስርአት እንዳይሰፍን እያደረገ ነዉ ሲሉ ዮሐንስ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። በክልሉ ያሉ ዜጎች በነፃነት ዲሞክራሲያዊ የመደራጀት መብታቸውን ተጠቅመው እንዳይደራጁ ለማድረግ ክልሉ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም አክለዋል። ቅጽ 2 ቁጥር 63 ጥር 9 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here