ታፍ ኦይል የአዉሮፕላን ነደጅ ማከማቻ ሊያስመርቅ ነው

0
1092

ታፍ ኦይል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በኢትዮጽያ አየር መንገድ ግቢ ውስጥ ያስገነባውን የአዉሮፕላን ነደጅ ማከማቻ በቀጣይ ማክሰኞ ጥር 19/ 2012 ሊስመርቅ ነዉ፡፡

ታፍ ኦይል ኢትዮጽያ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ዘመናዊ የሆነ እና ትልቅ የአዉሮፕላን ነዳጅ ማከማቻ ከነሙሉ አገልግሎቱ ሊስመርቅ እንደሆነ ለአዲስ ማለዳ በላከዉ መረጃ ገልጿል፡፡ በምርቃት መርሃ ግብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች፣ ሚኒስተሮች እና ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች በተገኙበት የምርቃት ፕሮግራሙና የምሳ ግብዣ በስካይ ላይት ኢንተርናሽናል ሆቴል ከቀኑ 7 ሰዓት የሚከናወን ተመላክቷል፡፡

በኢትዮጵያ ባለፈዉ በጀት ዓመት ስምንት መቶ ሀያ ሺ ቶን የአዉሮፕላን ነዳጂ አስገብታለች ለዚህም 15.4 ቢሊዮን ብር አዉጥታለ ፡፡ ታፍ ኦይል በ2002 ዓ.ም ስራ የጀመረ ሲሆን እስካሁን ድረስም የነዳጅ አስመጪነትን እና አከፋፋይነት ስራን አየሰራ ይገኛል፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 64 ጥር 16 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here