ኮካ ኮላ አዲስ ከአልኮል ነጻ መጠጥ ለኢትዮጵያ ገበያ አቀረበ

0
951

ኮካ ኮላ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነ ሽቴፕስ (Schweppes Novida Pineapple) የተሰኘ ከአልኮል ነጻ መጠጥ ለኢትዮጵያ ገበያ ሊያቀርብ ነው።
መጠጡ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ነው የተባለ ሲሆን፣ በአናናስ ጣዕም የቀረበ ከአልኮል ነጻ ማልት ነው። ምርቱ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መምጣቱ የአልኮል ተጠቃሚ ላልሆኑ ደንበኞች የተሻለ አማራጭ እንደሚሆን ተገልጿል።
ምርቱ ኮካ ኮላ በኢትዮጵያ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ለመጀመር እና መዋዕለ ነዋይ ለማፍሰስ ያለውን ፍላጎት የሚያሳይ መሆኑ ኮካ ኮላ ምርቱን ይፋ ባደረገበት ወቅት ገልጿል። ኮካ ኮላ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ 700 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠሩም ተጠቁሟል። አዲሱን ምርትም በቀጣይ ቀናት ለገበያ እንደሚያስተዋውቅ ይጠበቃል።
ኮካ ኮላ በዓለማችን በ200 አገራት ከ 500 በላይ የመጠጥ ሥያሜዎችን በባለቤትነት በማስተዳደር ላይ እንደሚገኝም ተጠቅሟል። ኮካ ኮላ በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት ምርቶቹን ሲያቅርብ ቆይቷል። የአምቦ የማእድን ውሃን ከፍተኛ የአክሲዮን ድርሻ በመግዛት በማስተዳደር ላይም ይገኛል። አምቦ የማዕድን ውሃ በ1922 የተመሠረተ ኩባንያ ሲሆን፣ መንግሥት ወደ ግል ባለቤትነት በተለያዩ ደረጃዎች ሲያስተላልፈው ቆይቷል።

ቅጽ 2 ቁጥር 66 ጥር 30 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here