የጠቅላይ ሚኒስትሩ ችግኝ መሰረቅ

0
702

ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ(ዶ/ር)ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኣባለት ለሚጠየቁት ጥያቄ ምላሽ ይሰጣሉ መባሉን ብዙዎች በጉጉት ሲጠበቁ የነበረ ጉዳይ ነው፡፡
እሳቸውም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በደንቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ስለታገቱት ተማሪዎች፣ስለ ጸጥታ ችግር፣ስለ ምርጫ፣የትግራይ ክልል ስለምን ይገለላል የሚሉ እና ሌሎችም ጥያቄዎች ከአባላለቱ ቀርቦላቸው ነበር፡፡
ጠቅላዩ በምላሻቸውም ከእርሳቸው በፊት የነበረው መንግሥት በውስብስብ ‘ኔትወርክ’’ ተይዞ እንደነበረ እና እርሳቸውም ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ ይህን ‘ኔትወርክ ለመበጣጠስ’ ጥረት ሲደረግ መቆየቱታቸውን ተናግረዋል፡፡
የትግራይ ክልል ተወላጆች በማንነታቸው እየተለዩ ከሥልጣን እንዲነሱ ተደርገዋል የተባለው ስህተት እንደሆነ መበግለፅ በአሁን ወቅት ከ10 በላይ ሚንስትር ዲኤታዎች አሉ፤ አንዳቸውም አልተነሱም፤ ሌላ ሚንስትር እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤም አልተነሱም። የትግራይን ሕዝብ ያገለለ መንግሥት በኢትዮጵያ ሊኖር አይችልም። እኛም እንዲሆን አንፈቅድም ቃል ገብተዋል።
ምርጫን በተመለከተም ለቀረበላቸው ጥያቄ ምርጫ ቦርድ ተጠሪነቱ ለምክር ቤቱ እንደመሆኑ ቦርዱን የእናንተው ስለሆነ ጠርታችሁ አናግሩት ብለዋል በምላቸው፡፡
በደንቡደሎ ዩኒቨርስቲ ስለታጉቱ ተማሪዎችስ ደግሞ ምን ይመልሱ ይሆን የሚለው ጉዳይ ኣጓጊ ነበር፡፡እሳቸውም ቦኮሃራም ሰዎችን ሲያግት ኃላፊነቱን እሱ እንደሚወስድ ያናገራል እዚህ ግን እስከ አሁን ኃላፊነቱን እውስዳለሁ ያለ እንደሌለ በመናገር፤ እገታውን ማን እንደፈመው እንኳን አለመታወቁንም አልሸሸጉም፡፡ባልተሟላ መረጃ መግለጫ መስጠት ስላልነበረብን ነው መረጃ ሳንሰጥ የቆየነው ሲሉም ለማብራራት ሞክረዋል ዐብይ አህመድ፡፡ ይልቁንም የተጎዳ ተማሪ የለም ተማሪ ያልሆኑ፤መኖሪያቸው ሌላ ቦታ የሆኑ ግን እገታውን እንደተቀላቀሉም ገልጸዋል፡፡
መፍትሄ እንዲገኝም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ከሰላም ሚኒስትር እና ከሁሉም የጸጥታ ኣካላት የተውጣጣ ኮሚቴ ምርመራ ላይ መሆናቸውን በመግለፅ ምርመራው ሲጠናቀቅ ለሕዝቡ ግልፅ እንሚሆን ነው የተናገሩት፡፡
ይህ ምላሻቸም ብዙ ሰዎች ዘንድ ‹‹አንጅት ላይ ጠብ የሚል ምላሽ አይደለም ዝም ብሎ የተድበሰበሰ ምላሸ ነው የሰጡት›› በማለት በማህበራዊ ትስስር ገፆችላይ ርዕሰ ጉዳይ ሆነው ሰንብተዋል፡፡
እንደውም ስለተተከሉት ችግኞች መፋጥት መናገራቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ምን ነክቷቸው ነው ይህ ጉዳይ አጀንዳ መሆን ነበረበት ሲሉም የጠየቁ ጥቂት አይደሉም፡፡
አንዳንዶቹማ የዐብይ አህድ ማላሽ ወቅቱንና ሁኔታን ያላገናዘበ ምላሻቸው ሲሆንባቸው ሃሳባቸውን በግጥም እንዲህ የጻፉም አልጠፉም፡፡
አንተ አበባ ጠፍቶብህ እና ልጅ ጠፍቶብን፤
አብረን ስንፈልግ ቀኑ ሌት ሆነብን፤
እባክህ ለውጠን
እኛ አበባ እንስጥህ አንተ ልጆች ስጠን
ይህ ግጥም በሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ(ዶ/ር) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሰጡን ምላስተከትሎ ከሰሞኑን በማሕበራዊ ትሥሥር ገጾች ላይ በስፋት ሲንሸራሸር የበነረ ጉዳይ ነው፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 66 ጥር 30 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here