10ቱ ወላጆች አዋቂ ልጆቻቸውን በገንዘብ የሚደግፉባቸው አገራት

0
734

የደረሱ ወይም አዋቂ የሚባሉ ልጆች እድሜያው ከ18 በላይ የሆኑ ናቸው። ታድያ እነዚህ ልጆች በሠለጠኑ አገራት በዚህ የእድሜ ክልል ሲደርሱ ከቤተሰብ ጫንቃ ወርደው ራሳቸውን እንዲችሉ ቢጠበቅም፣ እውነታው ግን ያ አይደለም። በተለያዩ የዓለም አገራት፣ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገራት ሊገምቱት በማይችሉት ሁኔታ፣ በቤተሰቦቻቸው ላይ ጥገኛ ሆነው የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙ ሰዎች ቁጥር ቀላል አይደለም።
በእርግጥ ወላጆች ልጆቻቸዉን ከማሳደግም አልፎ እድሜያቸዉ ከ18 ዓመት በላይ ቢሆንም፣ ራሳቸዉን ችለው እስኪወጡላቸው የገንዘብ ድጋፍ የማድረግ ኃላፊነት በቅድሚያ የሚጣልባቸው ናቸው። ስታቲስታ የተሰኘው ድረ ገጽ ብሪትሽ ባንክን ዋቢ አድርጎ ባቀረበው ዘገባ መሠረት፣ እድሜያቸዉ ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ ልጆቻቸዉን በገንዘብ ከሚደግፉ ብዙ ወላጆች ካሉቸው ዐስር አገራት ተርታ አረብ ኤምሬትስ በአንደኛ ደራጃ ላይ ተቀምጣለች።
ይህም ማለት በአረብ ኤምሬት 79 በመቶ የሚሆኑ ወላጆች አዋቂ ልጆቻቸዉን በገንዘብ ይደግፋሉ። በተመሳሳይ በተርታው ኢንዶኔዥያ 77 በመቶ በመሆን ስትከተል፣ ሜክሲኮና ማሌዥያ ሦስተኛ እና አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። በዐስርቱ ዝርዝር የተካተተ የአፍሪካ አገር ግን የለም።
በዚህ ዝርዝር ዐስረኛ ደረጃ ላይ አትካተት እንጂ አስራ አንደኛ ደረጃ ላይ አሜሪካ ተቀምጣለች። በአሜሪካ 26 በመቶ ወይም ከአንድ መቶ ወላጆች ውስጥ 26ቱ ልጆቻቸውን በገንዘብ የሚደጉሙ እንደሆኑ መረጃው ያሳያል።

ቅጽ 2 ቁጥር 66 ጥር 30 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here