መድረክ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ መተዳደሪያ ደንቡን አሻሻለ

0
694

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ከዚህ ቀደም አንድ የጥምረቱ አባል የሌላ ጥምረት አባል መሆን አይችልም የሚለውን የመተዳደሪያ ደንቡን አንቀጽ አሻሻለ።

ጥር 23/2012 በጠራው አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ደንቡን ያሻሻለው መድረክ፣ ለዚህ ውሳኔ መነሻ የጥምረቱ አባላት ይህ አንቀፅ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በጋራ እንዳይሠሩ እያገዳቸው መሆኑን በማንሳታቸው ነው ሲሉ የመድረክ ጸሐፊ ደስታ ዲንቃ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

ጠቅላላ ጉባኤው በዚህ ጉዳይ ላይ ብቻ ውሳኔ ማሳለፉን የተናገሩት ደስታ፣ የምርጫ ቦርድ ተወካይም በጉባኤው ተገኝተው መታዘባቸውን ተናግረዋል።
ትብብር ለዴሞክራሲያዊ ፌደራሊዝም የተሰኘው እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር፣ የኦሮሞ ፌደራሊሰት ኮንግረስ እና የኦሮሞ ብሔራዊ ፓርቲ አዲስ ጥምረት መስርተው ከምርጫ ቦርድ የምስክር ወረቀት ለማግኘት ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወሳል። ቦርዱም ኦፌኮ አባል የሆነበት መድረክ፣ መተዳደሪያ ደንብ መሥራች ፓርቲዎቹ የሌላ ጥምረት አባል መሆን እንደማይችሉ ስለሚገድብ፣ ይህ እንዲታይ መጠየቁ ይታወሳል።

ቅጽ 2 ቁጥር 69 የካቲት 21 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here